የበለዓም ጽሑፍ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

የበለዓም ጽሑፍሥነ ቅርስ1960 ዓ.ም. በዴር አላ፣ ዮርዳኖስ የተገኘ ጽሑፍ ነው። ጽሑፉ አራማያ በሚመስል ቋንቋ ሲሆን የቢዖር ልጅ በለዓም የነበየ ትንቢት ይናገራል።

ይህ አረመኔ ነቢይመጽሐፍ ቅዱስ በተለይም ኦሪት ዘኊልቊ ምዕ. 22-24 ስለሚጠቀስ፣ በሙሴና በኢያሱ ዘመን እንደ ኖረ ስለሚባል፣ ይህ ጽሑፍ ለሊቃውንቱ ዕጅግ በጣም ቁም ነገር ይሆን ነበር። ይሁንና በብሉይ ኪዳንንጉሥ ዳዊት አስቀድሞ ለነበሩት ሰዎች አንዳችም ቅርስ የለም በማለት ብዙዎቹ ስለሚያስመስሉ፣ በአብዛኛው ቸል ብለውታል። ስለዚህ ታዋቂነቱ በደንብ ገና አልተስፋፋም። በጠቀሱት ጥቂት ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ ጽሁፉ 840 ዓክልበ. ግድም ተሳለ።

የጽሑፉ ቃላት በቀይና በጥቁር ቀለሞች በአንድ ግድግዳ ላይ ተቀለሙ። ከምድር መንቀጥቀጥ የተነሣ ይህ ግድግዳ ፍርስራሽ ሆኖ ጽሑፉ በሙሉ ሊተረጎም ባይቻልም፣ ትልቁ ክፍል ግን ተተረጎማል። ትንቢቱም በመጨረሻው ዘመን ስለሚደርሰው የዓለም ጥፋት ነው። ትንቢቱ ለበለዓም የመጣው ከ«ኤሎሂም» ነው ሲል፣ ይህ ግን በሊቃውንቱ ሀሳብ ዘንድ እንደ ዕብራይስጥ «አምላክ» ማለት ሳይሆን፣ ማለቱ በብዙ ቁጥር «አማልክት» መሆን አለበት ይላሉ።