የብረት ዘመን

ከውክፔዲያ

የብረት ዘመን በ«ሦስቱ ዘመናት» አስተሳሰብ ከናስ ዘመን ቀጥሎ የነበረው ዘመን ነው። በአጠቃላይ እንደ ተለመደ ከ1200 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ያለው ዘመን ያመልክታል። በዚህ ዘመን አብዛኞቹ መሣርያዎችና እቃዎች የተሠሩ ከብረት (በአቃላጭ ተቀላቅለው) ነበር።

የብረት ዶቃዎች በጥንታዊ ግብጽ (ጥንታዊ መንግሥት 3000 ዓክልበ ያህል) ተገኝተዋል፤ እነዚህ ከተፈጥሮ በረቅ ብረት ተደቀደቁ እንጂ አቃላጮቻቸው ለብረት ቀለጣ በቂ ሙቀት አያሞቁም ነበር። የናስ ቀለጣ ግን (መዳብቆርቆሮ) ያውቁ ነበር።

የብረት ቀለጣ ምናልባት ከ1880 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ በሐቲ አገር ይታወቅ ነበር (ካሩም ይዩ)። ዳሩ ግን የብረት መሣርዮች በጅምላ ተሥረው የነሐስ እቃዎች የተኩ ከ1200 ዓክልበ. በፊት አልሆነም። ከ1200 ዓክልበ. በኋላ «የብረት ዘመን» ሊባል ይችላል። የብረት ጥቅም ደግሞ በአውሮፓ፣ በእስያና በአፍሪካ በሙሉ ከ400 ዓክልበ. በፊት ተስፋፋ። ዓረብ ብረት የሚባሉት ጠንካራ ብረት ውሁድ አይነቶች ከ300 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ከሕንድ አገር ታውቀዋል። ይህም ዓረብ ብረት በ1 ዓም ግድም በታንዛኒያ ይሠራ ጀመር፤ በአውሮጳ ግን ዓረብ ብረት ከ900 ዓም ያህል በፊት አልተሠራም።

የ«ሦስቱ ዘመናት» አስተሳሰብ በመጀመርያ በጥንት በተደረጀው ወቅት፣ «አሁን በብረት ዘመን ውስጥ ነን» የሚል አስተሳሰብ ነበር። ስለዚህ የብረት ዘመን ልክ መቼ እንደ ተጨረሰ አልተወሰነምና ልዩ ልዩ ሀሣቦች አሉ።

  • 1 ዓም ጨረሰ፣
  • 1000 ዓም ጨረሰ፣
  • እስከ የኢንዱስትሪ አብዮት (አዲስ ቴክኖሎጂ፣ 1750 ዓም. ግድም) ድረስ ቆየ፣ ወይም
  • መቸም አልጨረሰም፣ እቃዎች እስካሁን በብረት እየተሠሩ ነውና።