የብርሃን ስብረት
Appearance
የብርሃን ስብረት እምንለው የብርሃን ጨረር ካንድ ብርሃን አሳላፊ ወደ ሌላ አሳላፊ አካል ሲጓዝ የሚገጥመውን የመጉበጥ ሁናቴ የሚወክል ጽንስ ሃሳብ ነው። ይህ የመጉበጥ ሁናቴ በስኔል ህግ እንዲህ ሲባል በሒሳብ ቋንቋ ይገለጻል፦
እዚህ ላይ በብርሃኑ ጨረርና በአንደኛው ብርሃን አስተላላፊ አካል ቀጤ ነክ መካከል ያለውን ማዕዘን ሲዎክል ደግሞ በሁለተኛው አካል ቀጤ ነክና በብርሃኑ ጨረር መካከል ያለውን ማዕዘን ይወክላል። n1 እና n2 የብርሃን አስተላላፊዎቹ የስብራት ውድር ናቸው፣ n = 1 ለጠፈር ሲሆን n > 1 ደግሞ ለማናቸው ብርሃን አስተላላፊና በከፊል አስተላላፊ ቁስ አካሎች የሚሆን ነው።
አንድ ጨረር ከአንድ አካል ወጥቶ ወደሌላ አካል ሲገባ የጨረሩ የሞገድ ርዝመትና የብርሃን ፍጥነቱ ይቀየራል። ሆኖም ግን ድግግሞሹ ባለበት ይጸናል። ያ ጨረር ለሚገባበት አካል ገላ ቀጤ ነክ ካልሆነ የሞገድ ርዝመቱ ወይም ፍጥነቱ መቀየር ብርሃኑ እንዲጎብጥ ወይም አቅጣጭ እንዲቀይር ያደርገዋል። አንድ መኪና አንድ ጎን ጎማዎቹ ቀጥ ቢሉና ሌሎች ጎን ጎማዎቹ ቢሽከረከሩ ሳይወድ በግድ እንደሚታጠፍ ነው። የብርሃን አቅጣጫ መቀየር የብርሃን ስብረት በመባል ይታወቃል።