የብርሃን ነጸብራቅ

ከውክፔዲያ
ብርሃን በመስታወት ሲንጸባረቅ። የብርሃኑን መግቢያ ማዕዘንና መውጫ ማዕዘን ያስተውሉ

ብርሃን አንድ ቁስን ሲመታ የቁሱ አተሞች የተውሰነውን ብርሃን ውጠው የተቀረውን መልሰው በተለያየ አቅጣጫ ወደውጭ ይረጫሉ። ይህ ጉዳይ የብርሃን ነጸብራቅ ይሰኛል። ሆኖም ግን ገጽታቸው ልስልስ የሆኑ አካላት (ለምሳሌ መስታወት) በሚያስነሱት የሞገድ መጠላለፍ ምክንያት አብዛኛው ጨረራ እርስ በርሱ ይጣፋል። በዚህ መጠፋፋት ወቅት ጸንቶ የሚቀረው ብርሃኑ በአረፈበት ማዕዘን ትክክል ያለው የሞገድ ስብስብ ብቻ ነው። በሌላ አባባል፣ የአንድ ገጽታ ቀጤ ነክ ቢሰጠን፣ አራፊ የብርሃን ጨረር ከዚህ ቀጤ ነክ አንጻር ያለው ማዕዘን ነጸብራቁ ከቀጤ ነኩ ጋር ካለው ማዕዘን ጋር እኩል ነው። ለዚህ ምክንያቱ የሞገድ ጥልልፍ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ብርሃን በየብርሃን ስብረት አማካይነት ሊንጸባረቅ ይችላል። ይህ የሚሆነው አንድ የብርሃን ጨረር አንድን ቁስ ለማምለጥ ያለው ፍጥነት በቂ ሆኖ ሳይገኝ ሲቀር ነው። ጨረሩ የቁሱን ድንበር ከተወሰነ ማዕዘን በላይ በሆነ አቅጣጫ ሲመታ በጣም ከመሰበሩ የተነሳ ተመልሶ ወደ ቁሱ ይንጸባረቃል። ይህም አጠቃላይ ውስጣዊ ነጸብራቅ እሚባለው ነው። የአልማዝ ፈርጦች መጭለቅለቅ ከዚህ የተነሳ ነው።

ብርሃን በዘፈቀደ ሲንጸባረቅ ተበተነ(ዲስፐርሽን)ይባላል። ማለት አቅጣጫ የሌለው መፍካትን ለማሳየት ነው። የሰማይ ሰማያዊ ቀለም ከዚህ የብርሃን መበተን ይመነጫል። የደመናወተት ነጭነት እንዲሁ ብርሃን በውሃና በካልሲየም ስልተበተነ ነው።