የኖርማኖች ቀንበር

ከውክፔዲያ

«የኖርማኖች ቀንበር» በተለይ በ17ኛው ክፍለ ዘመንእንግሊዝ አገር ፖለቲካ አንዳንዴ የሚሰማ ዘይቤ ነው።

ፑሪታን ዘመን በአንዳንድ ወገን (ለምሳሌ የቆፋሪዎቹ መስራች ጄራርድ ዊንስታንሊ) አስተሳሰብ፣ ከኖርማኖች ወረራ (1058 ዓ.ም.) አስቀድሞ እንግሊዞች (አንግሎ-ሳክሶኖች) ቀና፣ ጻድቅ፣ እና በእኩልነት የኖረ ነገድ ሆነው ነበር። ኖርማኖች ከፈረንሳይ ከወረሩ በኋላ ግን መንግሥቱን በመያዛቸው የአገሩ መኳንንት ሆኑ፣ ኗሪ እንግሊዞች ግን ተራ ሕዝቦች ሆነው በኖርማኖች ሥር («የኖርማኖች ቀንበር») ተጨቆኑ። በዚሁ ሃሣብ የእንግሊዝ ንጉሥና የእንግሊዝ መንግሥት የኖርማኖች ተከታዮች እንደ ሆኑ ይታዩ ነበር።