የአለቃ ታየ ተረትናምሳሌዎች

ከውክፔዲያ

ሁለት የወደደ አንድ ያጣል ሎሌ መስሎ ቢሰሩ ጌታ መስሎ ይበሉ ላለፈው አይጠጠቱም ለሚመጣው አይበለጡም ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ ለሽማግሌ የሚያስተምር በውኃ ላይ ይጽፋል ለሕፃን የሚያስተምር በደንጊያ ላይ ይጽፋል ማሩን አምርሮ ወተቱን አጥቁሮ ቢነግርህ አትመን ሲመክሩት ያጠፋል ልጅ ሲታጠቡት ያድፋል እጅ ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል ስንዴ ቢፈትጉት ይነጣል ነገር ቢመረምሩት ይወጣል በሰም ያጣበቁት ጥርስ ቢስቁበት አያደምቅ ቢበሉበት አያደቅ በጆሮ ከሰሙት ባይን ያዩት በጋ ቢዳምን ይዘንብ ይመስላል ሽማግሌ ቢያጐብብ ይወጋ የመስላል ባፍ ላይ ይረሳል በመጣፍ ላይ ይወሳል ተንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ታፉ ነገር ሁሉ በመጀመሪያ ይከብዳል በኋላ እየቀለለ ይሔዳል አህያ በለስላሳ ምላሷ እሾህ ትበላለች አህያን ተላም ነድዋት እሜቴን ከማዝገም አዝሎ መሮጥ ይሻል እንደ ሰው በከተማ እንዳውሬ በጨለማ እንደ ጆሮ ትልቅ እንደ ዓይን ትንሽ የለም እንጀራን ከባድ ዋይን ከዘመድ አይብን ሲያዩት አጓቱን ጠገቡት እግረኛ የውሰደውን ፈረሰኛ አይመልሰውም አጥብቀህ ጎርሰህ ወደ ዘመድህ ተመለስ ከሊቃውንት ሊቅ የሰማዩን በመጣፍ የምድሩን ባፍ የሚያውቅ ካልቸኮሉ እንቁላል ይሔዳል በእግሩ ከመድረሷ ጎመን መቀንጠሷ ከመጣፍ ይበልጣል የመምር አፍ ከሴት ሆዳም የጋላ ወራሪ ይሻላል ከበሬ በሮች፣ ካህዮች አህያ ከእግዚያብሔር ወዲያ ፈጣሪ ከዳኛ ወዲያ መርማሪ ከከታም ቅሬ ትሻለኝ ያገሬ ከገጠር ቄስ የደብር እመበለት ትሻላለች ካጭር ምከር ከረጅም ውረር ከፍትፍቱ ፊቱ ከጠላው ማቶቱ ዐባይ ማደሪያ ያለው ግንድ ይዞ ይዞራል ዓይን ከማየት ጆሮ ከመስማት አይጠግቡም ዘሆን የዋለችበትን ትመስላለች የማይታዘዝ ሎሌ የማያስታርቅ ሽማግሌ ታስሮ እንደሚጮኽ አለሌ የሴት አፈኛ የበቅሎ መድን ትሆናለች የሴት ደንደሁራ ከባልዋ ሆድዋን ትፈራ የሰነፍ ልቡ ዓይኑ ነው የወታደር ወዳጅ እህለ ፈጅ የዘላን ወዳጅ እሳረ ፈጅ የጨዋ ልጅ በከተማ፣ የባለጌ ልጅ በውድማ የጨዋ አሮጌ ከደጀ ሰላም የባለጌ አሮጌ ከላም ያፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም ዘመድ ቢረዳዳ ችጋርም አይጎዳ ዘመድ ከዘመዱ አህያ ካመዱ ፈሪ ለባልንጀራው አይሸሽም ፈረሰኛ ሲሸሽ እግረኛን ምን አቆመው