የአሜሪካን ዶላር ኢንዴክስ
የአሜሪዳን ዶላር ኢንዴክስ የገበያ ውስጥ ዋጋ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማዋቅ ይጠቅማል። ብዙ አገሮች ያላቸውን ጥሬ እቃ ለሌላ አገር በሚሸጡበት ጊዜ ዋጋቸውን የሚተምኑት በአሜሪካን ዶላር ነው። የሚገዛውም አገር ሰው ዋጋውን የሚተምነው በዶላር ነው። ስለዚህ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ መጨመርና መውረድ የሌላውንም አገር የንግድ ውጤት አቅራቢ የዋጋ ተመን አብሮ ይዞት ይሄዳል። ከዚህም በላይ የአገሮችን መቀያየሪያ ገንዘብ እንደየአገሩ የኢኮኖሚ መጠን በትንሹም ቢሆን ከፍና ዝቅ በዶላሩ ምንዛሪ ላይ ያመጣል። በዚህም የተነሳ የአሜሪካንን ዶላር እንዴክስ መመልከት የሌላውንም አገር የንግድ ሁኔታና እንቅስቅሴ፣ የወርቅና የተለያዩ ማዕድናት እንዲሁም የጥሬ ሀብት ውጤት ስንት ሊያወጣ እንደሚችል ለመገመት ያስችላል።
ከአሜሪካን ዶላር ኢንዴክስ ሌላ ፤ ሌሎች የትላልቅ ካምፓኒ ኢንዴክሶችን በዚሁ አይነት ዘዴ ለመጠቀም ይቻላል። ምክንያቱም ዋነኛው የኮሞዲቲ ገበያ ላይ ንግድ፤ እንደማንኛውም የንግድ ዘርፍ፤ ትርፍ በብዛት ለማግኘትና ኪሳራን ለመቀነስ ሲሆን በኮሞዲቲ ንግድ ላይ ደግሞ የወደፊቱ ዋጋ ስንት ሊሆን እንደሚችል ለመገመትና ኪሳራን አስወግዶ አትራፊው ገበያ ይትኛው እንደሚሆን ለመጠራጠር የሌሎችን ካምፓኒ እንዴክስ መመልከት ይጠቅማል።
ከትላልቅ ካምፓኒ ኢንዴክሶች መካክል ከዝህ በታች ያሉት በኮሞዲቲ ኢንዴክስ አቅራቢነታቸው ታዋቂነት አላቸው።
- ጎልድማን ሣክስ ኮሞዲቲ እንዴክስ (GSCI)
- ዳውጆንስ ኤ.ጂ.አይ. ኢንዴክስ (DJ-AIGCI)
- ሮጀርስ እንተርናሽናል ኮሞዲት እንዴክስ (RICI)