Jump to content

የአጼ ሚናስ ዜና መዋዕል

ከውክፔዲያ
የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [1] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች በግዕዝና በፖርቱጊዝ ማንበብ ይችላላሉ

የአጼ ሚናስ ዜና መዋዕል በግዕዝ እንደተጻፈና በፍራንሲስኮ ማሪያ ወደ ፖርቱጋልኛ እንደተተረጎመ ፣ በ1888 በሊዝቦን ፖርቱጋል እንደታተመ ከጎን ቀርቧል። ዜና መዋዕሉ የአጼልብነ ድንግል ልጅ የነበሩትን የአጼሚናስን ዘመን የመዘገበ ሰነድ ነው። አጼ ገላውዲወስ ከፖርቱጋል ሰራዊት ጋር ሆነው ግራኝ አህመድን በጦርነት ካሸነፉ በኋላ የግራኝ ልጅ የነበረውን መሃመድን ሲማርኩ ከግራኝ ሚስት ድል ወንበሬ ጋር በመደራደር ወንድማቸው አጼሚናስ በምርኮ ከተላከበት ከየመን በምርኮ ልውውጥ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደረገ። አጼ ገላውዲወስ በጦርነት ሲሞቱ ወድማቸው አጼ ሚናስ ነገሱ። ለ6 አመት ከገዙ በኋላ በወባ በሽታ በ1563ዓ.ም. አረፉ።

  • ይህ በኢትዮጵያዊ አይን እማኝ የተመዘገበው ዜና መዋዕል በግዕዝ ስለሆነ ለማንበብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ግዕዝ ወይም ፖርቱጋልኛ በትክክል የሚያውቅ ሰው ወደ አማርኛ ቢተርጉመው ለአንባቢ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።