የከለዳውያን ዑር

ከውክፔዲያ

የከለዳውያን ዑር ወይም ዑር ከላውዴዎን (ዕብራይስጥ፦ אוּר כַּשְׂדִים /ኡር ከሥዲም/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አብርሃም የተወለደበት ከተማ ነበረ።

ኦሪት ዘፍጥረት 11:28 ዘንድ ታራ የአብርሃምን ወንድም ሐራንን የወለደበት አገር የከለዳውያን ዑር ነበር፣ በ11:32 ታራ ከአብራም፣ ሎጥሦራ ጋር ከከለዳውያን ዑር ወጥተው በካራን ተቀመጡ።

ኩፋሌ 10፡24 መሠረት «የከለዳውያን ዑር» በአርፋክስድ ወገን በኬሴድ ልጅ በዑር በ1687 አመተ አለም ተሠርቶ ነበር። ሴሮሕናኮርታራ ሁላቸው በዛ ይኖሩ ነበር።

በቀድሞው አይሁድአረብ ልማድ ግን «የከላውዴዎን ኡር» በስሜን መስጴጦምያ በ«ኡርፋ» (ኤደሣ) እንደ ተገኘ ይባላል። ሆኖም ይህ ቦታ «ኡርፋ» የሚለውን ስም ያገኘው በኋለኛ ዘመን (ከ300 ዓክልበ. በኋላ) መሆኑ ይታወቃል።

ሥነ ቅርስ ሊቅ ሌዮናርድ ዉሊ «የከላውዴዎን ኡር»ና በኤፍራጥስ ላይ በሱመር የነበረው ዑር አንድላይ እንደ ነበሩ አሳመነ።