የድንችና የእንቁላል ሰላጣ

ከውክፔዲያ

የድንችና የእንቁላል ሰላጣ - በ15 ደቂቃ ውስጥ የሚዘጋጅ

የሚያስፈልጉ ነገሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ስምንት እንቁላል
  • አንድ ትልቅ ድንች፣ የተከተፈ (በፈለጉት ቅርጽ መክተፍ ይቻላል)
  • ሁለት የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝኩኒ (Pickle relish)
  • አራት የሻይ ማንኪያ ድሬሲንግ ክሬም (miracle whip መጠቀም ይቻላል)
  • ሁለት የሻይ ማንኪያ ሰናፍጭ (mustard)
  • ቁንዶ በርበሬ ለጣዕም
  • የፈረንጅ ቃሪያ (ተቆራርጦ)

አዘገጃጀቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. እንቁላሎቹን ለመቀቀያ በተዘጋጀ ድስት ሁለት ሴንቲ ሜትር በላይ ውሃው እስኪሸፍነው ድረስ ውሃ መጨመር፤ በእሳት ላይ ከጣዱ በኋላ ወዲያው እንደፈላ እንቁላሎቹን አውጥቶ በትኩሱ ውሃ ውስጥ ለ15 ደቂቃ ማቆየት፡፡ ከ15 ደቂቃ በኋላ እንቁላሎቹን ከትኩሱ ውሃ አውጥቶ እስኪቀዘቅዝ ድረስ በቀዝቃዛ ውሃ ማለቅለቅ፤ የቀዘቀዙትን እንቁላሎች እኩል ለሁለት ከሰነጠቁ በኋላ አስኳሉን እያወጡ ከንጹሕ ሰሀን ላይ ማድረግ፤
  2. በተፈለገው ቅርጽ የተከተፈውን ድንች ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ድረስ በውሃ ማብሰል፤ የበሰለውን ድንች ውሃውን አጠንፍፎ ድንቹን ማቀዝቀዝ፤
  3. ንጹሕ ሰሀን በማዘጋጀት የእንቁላል አስኳሉን ከተፈጨው ዝኩኒ፣ ከሰናፍጭ፣ ድሬሲንግ ክሬም፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ማቀላቀል፤ የበሰለውን ድንችም ለሰሀን ውስጥ ጨምሮ በሹካ እያማሰሉ ማቀዝቀዝ፤ በመጨረሻም በመመገቢያ ሰሀን አዘጋጅቶ የድንችና እንቁላል ሰላጣውን በሰሀኑ ላይ ማድረግና ለመልክ የፈረንጅ ቃሪያውን ቆራርጦ ላዩ ላይ መነስነስና ለማዕድ ማቅረብ፤