የጻዛጋ እና ሓዛጋ ትውፊት

ከውክፔዲያ

የጻዛጋ እና ሓዛጋ ትውፊትአማርኛትግርኛ እና ግዕዝ የተቀናበረ መጽሐፍ ሲሆን ወደ ፈረንሳይኛ ተተርጉሞ በ1904ዓ.ም. በሮማ ከተማ በስዊድኑ ዮሐንስ ኮልሞዲን የታተመ መጽሐፍ ነው። ወደ ትግርኛ ተተርጉሞ በ1907 በፍሬ ወልዱ ኪሮስ የታተመው ዛንታን ጻዛጋን ሓዛጋን ይሰኛል። መጽሐፉ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ ጣሊያን ወረራ ድረስ ስለሓዛጋጻዛጋ እንዲሁም ስለ ሀማሴን የተነገሩ አፈ ታሪኮችን፣ የተዘፈኑ ዘፈኖችንና ትውፊቶችን ያቀናበረ ነው። እኒህ ትውፊቶች የተሰባሰቡት በፕሮፈሰር ኮልሞዲን መሪነት ባህታ ተስፋ ዮሐንስ በተባለ የጻዛጋ ወጣት ነበር[1]

የመጽሐፉን 144 ገጾች ለማንበብ ምስሉ ላይ ይጫኑ

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ እዝራ ገ/መድህን, The last dragoman: the Swedish orientalist Johannes Kolmodin as scholar, activist and diplomat ed. Elisabeth Özdalga,Swedish Research Institute in Istanbul, 2006 ኢንተርኔት