Jump to content

የፉንግ ግዛት

ከውክፔዲያ
የስናር ግዛት (፲፬፻፺፮-፲፰፻፲፫ ዓ.ም)

የፉንግ ግዛት በደቡብ ምስራቅ ሱዳን፣ በተለይ በስናር ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን የነበር፣ ኢትዮጵያን ያዋስን የነበር ንጉዛት ነው። ምንም እንኳ ስናር ውስጥ ብዙ የተከፋፈሉ ግዛቶች የነበሩ ቢሆንም፣ ፉንጎች ይህን የተሰባጠረ ግዛት በማዋሃድ ግዛቱን ለማቋቋም ችለው ነበር። ግዛቱ በተጠናከረበት ዘመን፣ በተለይ በውትድርናው መስክ እጅግ የተሳካለት ነበር። ስለሆነም ግዛቱ ወደ ኮርዶፋንባዩዳገዚራ እና ቡታና በመስፋት እስከ አልዶያን መቆጣጠር ደርሰው ነበር። በዚህ ምክንያት፣ የግብጽ ገዥ የነበሩትን ቱርኮችን እና በዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያ ነገስታትንም እስከ ማስጋት ደርሰው ነበር።

ነገር ግን በፉንጎች ዘንድ አንድ ንጉስ ሞቶ በሌላ ሲተካ፣ መተካካቱ ምንጊዜም ደም የሚያፋሥሥ ነበር። ሌላው ድክመታቸው የግዛቱ ክፍሎች በዘር እጅግ የተለያዩ ነበር። እነዚህ የውስጥ ቅራኔዎች እና ከግብጽ የቱርክ ገዥዎች በሚያደርጉት ተጽዕኖ ግዛቱ ተዳክሞ በ1813 ኦቶማኖች የግብጽ ግዛት እንዲሆን አድርገውት ነበር።

ነገሩ በእንደዚህ ሁኔታ ከቆየ በኋላ በ1948 ስናር የአሁኒቷን ሱዳን ተቀላቀለ።