ስናር

ከውክፔዲያ
ስናር ክፍለ ሃገር

ሰናር (አረብኛ: سنار Sannār) ከሱዳን 18 ዋልያት (ክፍለ ሃገሮች) መካከል አንዱ ነው። ይህን ክፍለ ሃገር፣ በሰሜን ገዳሪፍ፣ በምዕራብ ዋይት ናይል ግዛት፣ በደቡብ ብሉ ናይል ግዛት እና ደቡብ ሱዳን ፣ እንዲሁም በምስራቅ ኢትዮጵያ ያዋስኑታል። ዋናው ከተማ ሲንጋ ቢሆንም የክፍለ ሃገሩ ትልቅ ከተማ ግን ስናር ነው። ድንደር ብሔራዊ ፓርክ ከኢትዮጵያ ድንበር አጠገብ ባለው የግዛቱ ክልል ይገኛል።

የዚህ ክፍል ዋና መተዳደሪያ ግብርና ነው። የስኳር ፋብሪካ፣ የፍራፍሬ ምርት (ማንጎና ሙዝ)፣ ከአባይ ወንዝ ዳር የሚደረግ የመስኖ እርሻ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ይጠቀልላል።