የ2003 ዓ.ም. ፉኩሺማ አደጋ ውጤት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

መጋቢት ፪ 2003 ዓ.ም. አንድ የምድር መንቀጥቀጥ ጃፓንን መታ። ይህ ጹናሚ (ታላቅ ማዕበል) ፈጠረና ጹናሚው የፉኩሺማ ኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጉዳትና አደጋ ሠራ። ከዚህ የተነሣ ብዙ የኒውክሌር ጨረራ እስካሁን እየወጣ ነው።

ጨረራው እስካሁን በጃፓን ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ከቤቶቻቸው አሳድዷል። በፓሲፊክ ውቅያኖስ በሰፊ ክልል ምንም ዓሣ ወይንም የባሕር ሕይወት የለም። የተገኘውም ዓሣ ቢበላ በጨረራው ይበከላልና ለጤና መጥፎ ነው። ጨረራው በውኃ እስከ ካሊፎርኒያ ድረስ አሁን እየደረሰ ነው። የጨረራው ውጤት ለማከላከል በቴሮድም ላይ የኑክሌር ጨረራ መጥፎ ውጤት ለማከም፣ ሰዎች ፖታሼም አዮዲድ (የአዮዲንና የፖታሼም ውሑድ) ይጠቀማሉ።