Jump to content

የያሚና ልጆች

ከውክፔዲያ
(ከያሚናውያን የተዛወረ)
የ«ብኔ ያሚና» እና የ«ብኔ ስምኣል» ሥፍራዎች በ1673 ዓክልበ. ጠረፎች

የያሚና ልጆች (አካድኛበኒ ያሚና፣ «የቀኝ ወይም ደቡብ ልጆች») ከአሞራውያን ኻና አገር ሁለት ኗሪ ብሔሮች አንዱ ነበር። ሌላውም የስምኣል ልጆች (በኒ-ስምኣል፣ «የግራ ወይም ስሜን ልጆች») ተባለ።

በኒ-ያሚናማሪ ዙሪያ፣ በበሊኽ ወንዝ ና ወደ ምዕራብ ከአሌፖ ደቡብ እስከ ቃቱ ድረስ ተገኙ። የማሪ ነገስታት ግን ከስምኣል ልጆች ጋር ተዘመዱና ብዙ ጊዜ ከበኒ-ያሚና ጋር ይታገሉ ነበር። በተለይ ነገሥታት ያህዱን-ሊም (1723-1707 ዓክልበ.)፣ ያስማሕ-አዳድ (1694-1687 ዓክልበ.) እና ዝምሪ-ሊም (1687-1673 ዓክልበ.) በያሚና ልጆች ላይ ዘመቱ። ከ1685 እስከ 1683 ዓክልበ. ድረስ ዝምሪ-ሊም ከበኒ-ያሚና ጋር ተጣላ፣ ከዚያ በኋላ ግን ሰላም ሆነና ከበኒ-ስምአል ጋር ተስማሙ።

በኒ-ያሚና የበግ እረኞች ቢሆኑም አንዳንድ መንደርና ከተማ ደግሞ ይሠፍሩ ነበር። በነገሥታት ወይም «ዳዊዱም» ተገዙ፤ «መርሁም» («እረኛ») የተባለ ማዕረግ ንጉሡን የሚያገለግሉ ነበር።

ይህ ስያሜ «በን-ያሚና» ከዕብራውያን ነገደ ብንያም (ዕብራይስጥ /ቢንያሚን/ «የቀኜ ልጅ») ጋራ ግንኙነት እንደነበረው በአንዳንድ መምህር ታስቧል። በዚህ ዘመን የዕብራውያን ነገዶች በግብጽ ባርነት የተገኙበት ቢሆን፣ ሌሎች ሃቢሩ የተባሉት ጎሣዎች በዙሪያው ታውቀዋል፤ ዝምድናቸው ግን ተከራካሪ ነው። በመጽሐፈ ኩፋሌ 32:18 መሠረት፣ ዮሴፍ በግብጽ በሞተበት ወቅት (1827 ዓክልበ.) ዕብራውያን የወንድሞቹን ሬሳዎች ወደ ከነዓን አድርሰው ብዙዎችም ወደ ግብጽ ተመልሰው ጥቂቶቹ ግን ከነሙሴ አባት ዕብራንኬብሮን ቀሩ። ይህ አንዳንድ ዕብራዊ ወገን በከነዓን ቆይቶ ከግብጽ ባርነት እንዳመለጠ ይመሰክራል።