ይሁዳዊ-ሮማንስ ቋንቋዎች
Appearance
维=>ሐ | ይህ መጣጥፍ «የሳምንቱ ትርጉም» ነበር። (የካቲት 13 ቀን 1998 ተመረጠ።) |
ይህዳዊ-ሮማንስ ቋንቋዎች ከሮማንስ ቋንቋዎች የወጡት በአይሁዶችም የሚናገሩ ልሳናት ናቸው። የራሳቸው ቋንቋዎች ሆነው እስከሚቆጠሩ ድረስ ተለውጠዋል ማለት ነው።
- ይሁዳዊ-ካታላን (ወይም ካታላኒክ) በሰሜንና በምሥራቅ እስፓንያ እና በባሌሪክ ደሴቶች በ"ተሰወረ አይሁዳዊ ህብረተሠብ" ቅሬታ ሆኖ ይቆያል።
- ይሁዳዊ-አራጎንኛ በሰሜን እስፓንያ ቀድሞ ከ750 ዓ.ም. ጀምሮ ይናገር ነበር፡፡ በ1484 ዓ.ም. አይሁዶች ሁሉ ከእስፓንያ ከተባረሩ በኋላ ግን መናገሩ ቆመ፡፡
- ይሁዳዊ-ሮማይስጥ (ወይም ላዓዝ) በድሮው ሮማ መንግሥት የተናገረው ቀበሌኛ ነበር፡፡
- ይሁዳዊ-ፖርቱጊዝ (ወይም ሉሲታኒክ) በፖርቱጋል "ተሰወረ አይሁዳዊ ህብረተሠብ" ቅሬታ ሆኖ ይቆያል።
- ላዲኖ የእስፓንያ ዋና ይሁዳዊ ቀበሌኛ እስከ 1484 ድረስ ነበር፡፡ ከመበራረትቸው በኋላ በተበተኑት ህብረተሠብ ጥቅሙ ሳይቋረጥ ዛሬም አንደኛው ይሁዳዊ-ሮማንስ ቋንቋ ሆኖ ይገኛል፡፡
- ዛርፋቲክ (ወይም ይሁዳዊ-ፈረንሳይኛ) በስሜን ፈረንሳይ የታደገ ቀበሌኛ ነው፡፡ ዛሬ ግን አይሰማም፡፡
የነኚህ ቀበሌኞች እድገት በሙሉ ግልጽ አይደለም፡፡ ወይም በቀጥታ ከይሁዳዊ-ሮማይስጥ ታደጉ ወይም ከሮማይስጥ የታደጉት ሮማንስ ቋንቋዎች ተለይተው ከያንዳንዱ ተነሡ፡፡
ይሁዳዊ-ሮማይስጥ፣ ዛርፋቲክ፣ ሿዲት፣ እና ይሁዳዊ-አራጎንኛ ሁላቸው ዛሬ አይናገሩም። መጨረሻ የሿዲት ተናጋሪ በ1969 ዓ.ም. ዐረፉ።
ይሁዳዊ-ፖርቱጊዝ እና ካታላኒክ ቅሬታዎች ብቻ ሆነው ቆይቷል።
'ኢታልኪያን' 2 ትውልዶች በፊት በ5000 ኢጣልያዊ-አይሁዶች ተናግሮ ዛሬ ግን በ200 — በተለይ ባረጁ — ሰዎች ዘንድ ብቻ ይሰማል።
ላዲኖ በ150,000 ተናጋሪዎች መሃል እስካሁን ይሰማል። እነዚህ የሚኖሩ በተለይ በስሜን አፍሪካ እና በቱርክ ነው። አብዛኞቹ ሌላ ቋንቋ ደግሞ ይችላሉ።
የነዚህ ቋንቋዎች ወደፊት እርግጠኛ አይደለም። ዛሬ ዕብራይስጥ እንደገና በሰፊ ስለሚጠቅም፣ ወይም ወጣቶቹ የየአገራቸውን ቋንቋውች (እንደ ቱርክኛ) መጀመርያ ስለሚማሩ፣ ሁኔታው ብዙ ተስፋ አይሰጥም።