ዶናልድ ጆን ትራምፕ

ከውክፔዲያ
ዶናልድ ትራምፕ
ባለቤት ኢቫና ትራምፕ (ከእ.ኤ.አ. 1977-1991)
ማሪያ ሜፕልስ (ከእ.ኤ.አ. 1993-1999)
ሜላኒያ ትራምጵ (ከእ.ኤ.አ. 2005 ጀምሮ)
ልጆች ከዜልኒኮቫ
ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር
ኢቫንካ ትራምፕ
ኤሪክ ትራምፕ
ከሜፕልስ
ቲፋኒ ትራምፕ
ከኖውስ
ባሮን ትራምጵ
አባት ፍሬድ ትራምፕ
እናት ሜሪ አን ማክሊኦድ
የትውልድ ቦታ ክዊንስ ኒውዮርክ ከተማ
የተወለዱት እ.ኤ.አ ጁን 14 1946
ሀይማኖት ፕሪስባይቴሪያኒዝም
ፊርማ የ{መለጠፊያ:ስም ፊርማ


ዶናልድ ጆን ትራምፕ (ጁን 14 ቀን 1946 እ.ኤ.አ. ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል።

በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ዘ አፕሬንቲስ የተባለ ፕሮግራምን በኤን ቢ ሲ ላይ ያቀርብ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የሪፎርም ፓርቲ እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ ቴድ ክሩዝ እና ጆን ካሲች ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።

በፖሊሲው «የጉዞ ማገጃ» በተመለከተ የ፰ቱ አገራት ብቻ እነርሱም እስላማዊው መንግሥት መሬት የያዙባቸው ወይም አክራሪነት የበዛባቸው ስምንት አገራት ዜጎች ላይ ተጣለ።

ነገር ግን በጥር 2010 ዓም (18 January፣ 2018 እ.ኤ.አ.) ሃይቲ (የእስላማዊ መንግሥት አገር ባትሆንም) ዜጎችዋ ቪዛ ለማይቀበሉት አገራት ተጨመረች።

ቀደምት የሕይወት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዶናልድ ትራምፕ ከኒው ዮርክ ከአምስቱ ቀጠናዎች አንዱ በሆነው በክዊንስ በእ.ኤ.አ. ጁን 14 1946 ተወለደ። ለእናቱ ሜሪ አን እና ለአባቱ ፍሬድ ትራምፕ ከአምስት ልጆች መሃል አራተኛው ልጃቸው ነበር። እናቱ የተወለደችው በስኮትላንድ ሉዊስ ኤንድ ሃሪስ ደሴት ላይ ቶንግ በተባለው ስፍራ ነው። በእ.ኤ.አ. 1930 በ18 ዓመቷ ዩናይትድ ስቴትስን ጎበኘች እናም ከፍሬድ ትራምፕ ጋር ተገናኘች። በእ.ኤ.አ. 1936 ትዳር ይዘው በጃማይካ ኢስቴትስ ክዊንስ መኖር ጀመሩ። በዚህም ስፍራ ፍሬድ ትራምፕ ታላቅ የሪል ኢስቴት ገንቢ ሆኖ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ፥ ሮበርት የተባለ አንድ ወንድም፣ ሜሪአን እና ኤሊዛቤት የተባሉ ሁለት እህቶች አሉት። ፍሬድ ጁኒየር የተባለ ወንድሙ ደግሞ ከአልኮል ሱስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል ፤ ይህም ከአልኮሆል መጠጥ እና ከትምባሆ እንዲታቀብ እንዳደረገውም ዶናልድ ትራምፕ ይናገራል።

የዶናልድ ትራምፕ አባት ከካልሽታት ጀርመን በስደት ከመጡት ከፍሬድሪክ እና ከኤሊዛቤት ትራምፕዉድሄቨን ክዊንስ ተወለደ። ዶናልድ ትራምፕ በእ.ኤ.አ. 1976ቱ የኒው ዮርክ ታይምስ የሕይወት ታሪክ መዛግብት ላይ እንዲሁም በእ.ኤ.አ. 1987 በታተመው ዘ አርት ኦፍ ዲል በተሠኘው መጽሐፉ ውስጥ በተሳሳተ መልኩ ፍሬድሪክ የስዊድን ዝርያ እንዳለው ገልጿል። ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ የቤተሰብ ታሪክ ጸሐፊ ነው ብሎ የጠራው የወንድም ልጅ እንዳለው ከሆነ ፍሬድሪክ ትራምፕ ይህንን አቋም ለረጅም ጊዜያት የያዘው "ብዙ አይሁዳዊያን ጓደኛሞች ስለነበሩት እና ጀርመናዊ መሆን ጥሩ ስላልሆነ ነበር" ነው ብሏል። ኋላ ግን ዶናልድ ትራምፕ በቅድመ አያቶቹ ጀርመን መሆኑን አምኖ በእ.ኤ.አ. 1999 በኒው ዮርክ ከተማ በተካሄደው በጀርመን - አሜሪካን ስቱበን ሰልፍ ላይ በግራንድ ማርሻልነት አገልግሏል።

References[ለማስተካከል | ኮድ አርም]