ጀበና

ከውክፔዲያ

ጀበና ኢትዮጵያ ውስጥ ለቡና ማፍያ የሚያገለግል ከሸክላ የሚሰራ አንገት ያለው ከስሩ ክብ የሆነ፣ ከጎኑ ደግሞ ሹል የሆን ማንቆርቆሪያ አፍ ያለው፣ ባብዛኛው ጠቆር ያለ መልክ ያለው እቃ ነው።

የጀበና አሰራር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ የሚሰራውም በሸክላ ሰሪዎች ነው፤ በመጀመሪያ በጭቃ ተሰርቶ ይደርቃል፤ ከዚያ ይወለወላል፤ ከዚያ ይተኮሳል፤ ተተኩሶ ወይም በሳት ነዶ አፈር ይመስላል። በሸክላ ሰሪዎች ለገበያ ይቀርባል። ከዚያ ተጠቃሚዎች በእሳት ለብልበው ጥቁር ቀለም ይይዛል። በመጨረሻ በስራ ይውላል።

ተጨማሪ ማስረጃ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]