Jump to content

ጉብር ትንታኔ

ከውክፔዲያ
የኪርኮፍ ጅረት ህግ ለጉብር ትንታኔ መሰረት ነው።
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

ተመልከት · ውይይት · ቀይር


ጉብር ትንታኔኤሌክትሪክ ዑደትን ለመተንተን እና በእያንዳንዱ የኤሌክትሪክ ጉብር (መጋጠሚያ ነጥብ) ላይ ያለን የኤሌክትሪክ እምቅ አቅምን ለማስላት የሚረዳ የሥነ ኤሌክትሪክ መሰረታዊ መሳሪያ ነው። በሌላ አነጋገር፣ ጉብር ትንታኔ የአንድ ኤሌክትሪክ ዑደት ቅርንጫፍ ጅረትንና ቅርንጫፍ ቮልቴጅ በመጠቀም የዚያን ነጥብ ቮልቴጅ ከአንድ በነሲብ የተመረጠ ጉብር አንጻር የምናሰላበት ዋና መሳሪያ ነው።

የጉብር ትንታኔ ደረጃ በደረጃ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1. የኤሌክትሪክ ዑደቱ ሽቦዎች እሚጋጠሙባቸውን ነጥቦች በሙሉ ንቅሰህ አውጣ። እኒህ መጋጠሚያዎች ጉብር (ኖድ) ይባላሉ።

2. ከነዚህ ጉብሮች አንዱን በነሲብ መርጠህ ዋቢ ጉብር (ማነጻጸሪያ ጉብር) አድርግ።

የዋቢ ጉብሩ ማናቸውም ነጥቦች ሊሆን ይችላል። ለመስሉ ለውጥ አያመጣም። ሆኖም ብዙ ሽቦዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተገናኙትን ጉብር መምረጥ ትንታኔውን ያቃልላል።

3. ቮልቴጃቸው የማይታዎቁቱን ሁሉን ጉብሮች ስም ስጥ። ቮልቴጁ እሚታዎቀውን ጉብር መሰየም አስፈላጊ አይደለም።

4. ለእያንዳንዱ የማይታዎቅ የጉብር ቮልቴጅ ፣ የኪርኮፍ ጅረት ህግን በመጠቀም የጅረት ፍሰቱን እኩልዮሽ ጻፍ።

በሌላ አነጋገር፣ ከየጉብሩ የሚዎጡት ሁላቸውም ጅረቶች ሲደመሩ ዜሮ ይሆናሉ።
በሁለት ጉብሮች መካከል የሚፈሰው ጅረት እሚሰላው "ከአለንበትን ጉብር ቮልቴጅ ላይ የሌላውን ጉብር ቮልቴጅ በመቀነስ፣ ውጤቱን በመካከል ለሚገኘው ተቃዋሚ በማካፈል የሚገኝ ነው።

5. በሁለት ቮልቴጃቸው የማይታወቁ ጉብሮች መካከል የቮልቴጅ ምንጭ ካለ፣ ሁለቱን ጉብሮች አንድ ላይ በመጭመቅ ሱፐር ጉብር ፍጠር። የሁለቱ ጉብሮች ጅረት በአንድ እኩልዮሽ ይጠቃለልና አዲስ የቮልቴጅ እኩልዮሽ ይጻፋል።

6. ከኒህ ደረጃዎች በኋላ የሚፈጠረውን የሳይመልታኒየስ እኩልዮሽ ስርዓት፣ በሒሳብ ፈተህ፣ የጉብሮቹን ቮልቴጅ አግኝ።

አንድ ያልተወቀ ቮልቴጅ, V1.


በዚህ ዑደት ያልታወቀው ቮልቴጅ V1 ብቻ ነው። በዚህ ዑደት ሦሥት ግንኙነቶች ሲኖሩ፣ ሦስት ጅረቶች ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው። የነዚህ ጅረቶች አቅጣጫ ከጉብሩ ወጥተው እንደሚፈሱ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በመነሳት

  1. በተቃዋሚ R1 የሚፈሰው ጅረት እንዲህ ይሰላል: (V1 - VS) / R1
  2. በተቃዋሚ R2 የሚፈሰው ጅረት እንዲህ ይሰላል: V1 / R2
  3. በጅረት ምንጭ IS ውስጥ የሚፈሰው ጅረት ደግሞ: -IS ነው


የኪርኮፍ ጅረት ህግን በተጠቀሰው ጉብር ላይ ስንተገብር:


ይህን እኩልዮች ከ V1 አንጻር ስንፈታ:


ለተጠቀሱት ተለዋዋጮች የተሰጡትን የቁጥር ዋጋዎች ከላይ ባገኘነው እኩልዮሽ ስንተካ ውጤቱ እንዲህ ይሆናል