የአነባብሮ እርግጥ

ከውክፔዲያ
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

ተመልከት · ውይይት · ቀይር


የአነባብሮ እርግጥ ከአንድ በላይ የሆኑ ራሳቸውን የቻሉ የጅረት ወይንም ቮልቴጅ ምንጮች በአንድ የ ኤሌክትሪክ ዑደት ውስጥ ሲገኙ፣ የሚፈጠረውን የስሌት ውስብስብነት ለመቀነስ የሚረዳ ነው። ምንም እንኳ የአነባብሮ እርግጥ በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ቢሆንም፣ የሚተገበርበት የኤሌክትሪክ ዑደት አይነት ከጉብር ትንታኔ ይጠባል። ይሄውም፣ የአነባብሮ እርግጥን ለመጠቀም፣ የሚተነተነው ዑደት ሊኒያር መርብ መሆን አለበት።

የአነባብሮ እርግጥ እሚለው እንዲህ ነው፡ አንድ ሊኒያረ የኤሌክትሪክ ዑደት ውስጥ ከአንድ በላይ ራሳቸውን የቻሉ የጅረት ወይንም የቮልቴጅ ምንጮች ሲገኙ፣ የአጠቃላይ ዑደቱ ውጤት ልክ እያንዳንዳቸው ምንጮች ለየብቻቸው በዑደቱ ላይ ቢገኙና፣ የሚያስገኙት ውጤት ከተሰላ በኋላ በተናጠል የሚገኙትን ውጤቶችን በመደመር (በማነባበር) የአጠቃላይ ዑደቱን ውጤት ማስገኘት ይቻላል። በዚህ ወቅት እያንዳንደቸው ምንጮች ከስሌት ሲገለሉ በዜሮ ዋጋና በውስጣቸው ባለ ተቃውሞ ይተካሉ።

የአነባበሮ እርግጥ ደረጃ በደርጃ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ከአንድ የቮልቴጅ ወይንም ጅረት ምንጭ በስተቀር፣ በዑደቱ ውስጥ የሚገኙትን ማናቸውንም ምንጮች አጥፋ። (በዜሮ ተካ)።
  2. የጠፉትን ራሳቸውን የቻሉ የቮልቴጅ ምንጮች በዜሮ ተቃውሞ ወይንም በሾርት ተካ።
  3. የጠፉትን ራሳቸውን የቻሉ የጅረት ምንጮችአዕላፍ ተቃውሞ (ኦፕን) ተካ።
  4. ከላይ የተጠቀሱትን ደረጃዎች ለእያንዳንዳቸው ምንጮች በተናጥል ተግብር።
  5. ከነዚህ ደረጃዎች በኋላ የሚገኙትን ውጤቶች ደምር። ድምሩ የአጠቃላዩ ዑደት ውጤት ይሆናል።

የአነባብሮ እርግጥ ትንታኔ በዑደት ትንታኔ ውስጥ በጣም ጠቃሚ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ማናቸውንም ዑደቶች ወደ ኖርተን እኩያው እና ቴቭኒን እኩያው ለመቀየር ይረዳልና።