አቃቢነት

ከውክፔዲያ
ሙላት እንደ የቮልቴጅ ርክብ ግራፍ - የግራፉ ኩርባ እንደሚያሳየው አቃቢነቱ 200 pikofarad ፒኮፋራድ ነው።
ሙላቶች በአቃቢው ውስጥ ሲጠራቀሙ። በሁለቱ ሳህኖች መካከል የኤሌክትሪክ መስክ ይፈጠራል። አቃቢ እንግዲህ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ሲሆን የሚያጠራቅመው የኤሌክትሪክ ሙላት እላዩ ላይ ከሚፈጠርበት የቮልቴጅ ጫና ጋር ተመጣጣኝ ነው
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

ተመልከት · ውይይት · ቀይር


አቃቢነት ወይንም ካፓሲታንስ የሚለካው የአንድ ቁስን የኤሌክትሪክ ሙላት (ቻርጅን) የማጠራቀም ችሎታ ነው። የበለጠ ትክክል ለመናገር አንድ ቁስ ላይ በሚያርፍ የቮልቴጅ ጫና ምክንያት ያ ዕቃ ሊያጠራቅመው የሚችለው የኤሌክትሪክ ሙላት መጠን የዚያ ቁስ አቃቢነት ይባላል። ስለሆነም አቃቢነት በአንድ ቁስ ውስጥ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ሙላት እዚያ ዕቃ ላይ በተጫን ቮልቴጅ ሲካፈል ይገኛል፡፡ በሒሳብ ቋንቋ፦

መለኪያውም ፋራድ farad ሲሰኝ 1 ፋራድ 1 ኩሎምብ ሙላት በ1 ቮልት ማለት ነው።

አቃቢነት በኤሌክትሪክ ዑደት ስራ ላይ ተፈላጊ እንዲሁ ያልተፈለገ ባህሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እራሳቸውን ይቻሉ አቃቢዎች በተፈለገው መጠን ዑደቱ ውስጥ ይገባሉ።

አቃቢዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አንድ አቃቢ ለመስራት የሚያገለግሉ ኤሌክትሪክ አስተላላፊዎች፣ ጂዎሜትሪያቸው ከታወቀና በነዚህ አስተላላፊዎች መካከል ያሉ ኤሌክትሪክ አጋጅዎች የ ዳይኤሌክትሪክ ጸባይ ቁጥር ከታወቀ የአቃቢው ዋጋ ምን ሊሆን እንዲችል መተንበይ ይቻላል። ለምሳሌ የ"ትይይዩ ሳህን" አቃቢን ብንወስድ፣ ሳህኖቹ ስፋታቸው A ቢሆን፣ በመካከላቸው ያለው ክፍተት ርዝመት d ቢሆን፣ ከኒህ ሳህኖች የተሰራ አቃቢ ዋጋው እንዲህ ይሰላል

እዚህ ላይ

C አቃቢነት ሲሆን
A የሁለቱ ሳህኖች ንብብር ስፋት
εr በሁለቱ ሳህኖች መካከል ያለው ቁስ አንጻራዊ ቋሚ አስተላላቲፍነት ( ወይንም ዳይኤሌክትሪክ ቁጥር) ነው። ( ይህ ቁጥር ለኦና εr= 1 ዋጋ አለው)
ε0ኤሌክትሪክ ቋሚ ቁጥር (ε0 ≈ 8.854e^-12uF m–1) ሲሆን
d ደግሞ በሁለቱ ሳህኖች መካከል ያለ ክፍተት ነው።

አቃቢነት እንግዲህ ከሳህኖቹ ተነባባሪ ስፋት ጋር እኩል ሲያድግ፣ በሳህኖቹ መካከል ከሚፈጠረው ክፍተት ርዝመት አንጻር የተገላቢጦች ያድጋል ማለት ነው።

በአቃቢ ውስጥ ሙላት ሲጠራቀም፣ አቅም ም ይጠራቀማል። የዚህ የተጠራቀመ አቅም መጠን እንዲህ ይሰላል፦

.

W የተጠራቀመው አቅም ሲሆን ; C አቃቢነት; እና V ቮልቴጅ ናቸው።

የተለያዩ የአስተላላፊ ቅርጾች የተለያዩ አቃቢነት እንዳላቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ስም አቃቢነት መጠን ምስል
ሳህን አቃቢ
ኮአክሲያል ኬብል
ሉል አቃቢ
ኳስ አቃቢ,
ትይዩ ሽቦዎች
ሽቦና ወለል
d > R


ተጨማሪ ንባብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • (እንግሊዝኛ)Tipler, Paul (1998). Physics for Scientists and Engineers: Vol. 2: Electricity and Magnetism, Light (4th ed.). W. H. Freeman. ISBN 1-57259-492-6
  • (እንግሊዝኛ)Serway, Raymond; Jewett, John (2003). Physics for Scientists and Engineers (6 ed.). Brooks Cole. ISBN 0-534-40842-7
  • (እንግሊዝኛ)Saslow, Wayne M.(2002). Electricity, Magnetism, and Light. Thomson Learning. ISBN 0-12-619455-6. See Chapter 8, and especially pp. 255–259 for coefficients of potential.