Jump to content

የኖርተን እርግጥ

ከውክፔዲያ
(ከኖርተን እርግጥ የተዛወረ)
በጥቁሩ ሳጥን ውስጥ የሚታዩት የተወሳሰቡ የጅረት ምንጮች፣ የቮልቴጅ ምንጮች እና የቅዋሜዎች ቅንብር በኖርተን እርግጥ መሰረት እቀኝ በሚታየው መልኩ በአንድ ቅዋሜና ከርሱ ትይዩ ባለ በአንድ የጅረት ምንጭ ይተካሉ
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

ተመልከት · ውይይት · ቀይር


የኖርተን እርጉጥ የተወሳሰቡ የኤሌክትሪክ ኡደቶችን ለማቃለል የሚረዳ ስሌት ነው። እርግጡ እንደሚለው፣ ማናቸውም የምንጮች ኤኤክትሪክ ጅረት ምንጮች እና ኤሌክትሪክ ተቃውሞወች ጥምረት፣ በተመጣጣኝ ሁኔታ በአንድ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጭ እና ከርሱ ትይዩ ባለ የኤሌክትሪክ ተቃዋሚ ሊተካ ይችላል።

በአንድ አይነት ብቻ የሚደጋገም ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ስርዓት እንዲሁ በኖርተን እርጉጥ መሰረት በተመጣጣኝና ቀላል የኤሌክትሪክ ዑደት ሊተካ ይችላልል። በዚህ ወቅት እርጉጡ ለኤሌክትሪክ ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን እንደ ካፓሲተር እና ኢንደክተር ላሉ የኢምፒደንስ አይነቶችም ይሰራል።

የኖርተን እርጉጥ ስሌት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1. መጀመሪያ የኖርተን ኤሌክትሪክ ጅረትን INo አግኝ።

ይህን ለማድረግ አንድ የኤሌክትሪክ ስርዓት እጫፎቹ A እና B ላይ ጭነት ቢደረግበት ያን ጭነት ማውረድና በምትኩ ዑደቱን እዚያ ቦታ ላይ መዝጋት ያስፈልጋል። ከዚያ በተዘጋው መስመር ላይ የሚፈሰውን የኤሌክትሪክ ጅረት IAB ማስላት የኖርተን ጅረት INo ን ይሰጣል።

2. ቀጥሎ የስርዓቱን ኖርተን ቅዋሜውን RNo አግኝ።

ኢ-ጥገኛ ምንጮች ብቻ ላሉዋቸው ዑደቶች የሚሰራ
በAB መካከል ያለውን ቮልቴጅ መጀመሪያ ማግኘት። ይሄውም የሚሆነው በAB ላይ ያለን ጭነት በማውረድና ዑደቱን በመክፍተ በሁለቱ ጫፎች መካከል ያለውን ቮልቴጅ AB በመለካት ነው። RNo እንግዲህ VAB ለ INo. ሲካፈል ነው ማለት ነው።
ወይንም እንዲህ ማስላት ይቻላል፦
ኢጥገኛ የሆኑ የቮልቴጅ ምንጮችን በዝግ ዑደት መተካት እና የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮችን በክፍት ዑደት መተካት። ክAB አንጻር የሚሰላው አጠቃላይ ኤሌክትሪክ ቅዋሜ የኖርተን ቅዋሜ RNo. ነው ማለት ነው።
ወይንም
የቴቭኒን ተቃውሞው ክተሰጠ ከኖርተን ተቃውሞ ጋር እኩል ስለሆነ የቴቭኒኑን ቅዋሜ መውሰድ።
ጥገኛም ሆነ ኢጥገኛ ምንጮች ላሉዋቸው ዑደቶች የሚሰራ አጠቃላይ ስሌት
AB ላይ ቋሚ የሆነ የጅረት ምንጭ ይሰካል። ይህ ምንጭ 1 Ampere ጅረት ያመነጫል። ይህ ከሆነ በኋላ በAB መካከል ያለው ቮልቴጅ ይለካል። ቮልቴጁ ለ1 Ampere ሲካፈል የኖርተን ቅዋሜው RNo ተገኘ ይባላል።
መፍትሄ ደረጃ 0: የመጀመሪያ የተሰጠ ውስብስብ ዑደት
መፍትሄ ደረጃ 1: ተመጣጣኝ ወጭ የኤሌክትሪክ ጅረት ስሌት
መፍትሄ ደረጃ 2: ተመጣጣኝ ቅዋሜ ስሌት
መፍትሄ ደረጃ 3: ተመጣጣኝ የኖርተን ዑደት

በምሳሌው ላይ አጠቃላይ ጅረት Itotal እንዲህ ይሰላል

በጭነቱ ውስጥ ሊያልፍ የሚችለው ጅረት በጅረት ማካፈያ ህግ መሰረት እንዲህ ይሰላል:

ከክፍቱ የጭነት ማስቀመጫ ወደ ኋላ ስንመለከት የሚገኘው ተመጣጣኝ ቅዋሜው እንዲህ ይሰላል:

ስለሆነም ተመጣጣኙ የኖርተን ዑደት 3.75 mA ጅረትና ከርሱ ትይዩ 2 kΩ ቅዋሜ አለው ማለት ነው።

ከቴቭኒን ወደ ኖርተን አቀያየር ዘዴ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኖርተን ተመጣጣኝ ኡደት ከ የቴቭኒን ተመጣጣ ዑደት ጋር እንዲህ ይዛመዳሉ፡

የውጭ ማያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]