Jump to content

ኤሌክትሪክ ዑደት

ከውክፔዲያ
(ከየኤሌክትሪክ ዑደት የተዛወረ)
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

ተመልከት · ውይይት · ቀይር
ቮልቴጅ ምንጭና ከኤሌክትሪክ ተቃዋሚ የተሰራ ቀላል የኤሌክትሪክ ዑደት። በኦኽም ህግ መሰረት , V ቮልቴጅ ሲሆን i የኤሌክርኪክ ጅረትና R የኤሌክትሪክ ተቃውሞ መጠን ናቸው

ኤሌክትሪክ ዑደት ማለቱ የኤሌክትሪክ አባላት እርስ በርስ ግንኙነት ነው። የኤሌክትሪክ አባላት (የኤሌክትሪክ መሰረታዊ ክፍሎች) ኤሌክትሪክ ተቃዋሚን፣ ኤሌክትሪክ ቃቤን፣ ኤሌክትሪክ አቃቤን፣ ቮልቴጅ ምንጭን፣ ኤሌክትሪክ ጅረት ምንጭማብሪያ ማጥፊያንና ሽቦን ይጠቀልላል። በኤሌክትሪክ መረብና በኤሌክትሪክ ዑደት ያለው ልዩነት የኤሌክትሪክ ዑደት ሽቦወች የተዘጋ መንገድ ሲሰሩ የኤሌክትሪክ መረብ ግን ክፍት ሊሆን ይችላል። በሌላ አነጋገር በኤሌክትሪክ ዑደት ውስጥ የሚፈጠር የኤሌክትሪክ ጅረት ክብ ሰርቶ ይመላለሳል እንጂ ወጥቶ የሚጠፋበት ክፍተት አያገኝም።

ከቮልቴጅ ወይንም ጅረት ምንጮች፣ ከጉልት የኤሌክትሪክ አባላት (ፓሲቭ ኤለመንትስ - ምሳሌ ተቃዋሚ፣ አቃቤና ቃቤ)፣ ከቀጥተኛ የተበተኑ አባላት (የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦ) የተሰሩ ማናቸውም የኤሌክትሪክ መረቦች በአልጀብራና ሽግግር (ላፕላስ ሽግግርፎሪየር ሽግግር ወዘት...) መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተተንትነው በቀጥተኛ ጅረት (ዲሬክት ከረንት)፣ በአመንቺ ጅረት (ኦልተርኔቲንግ ከረንት)ናቅጽበታዊ ባህርይ የሚያሳዩትን ጸባይ ማስላት ይቻላል።

ተነሳሽ የኤሌክትሪክ አባላትን (አክቲቭ ኢለመንትስ) ያቀፉ የኤሌክትሪክ ዑደቶች ባንጻሩ ኤሌክትሮኒክ ዑደት ሲሰኙ፣ ትንታኔያቸው ጉልት የኤሌክትሪክ አባላት (ፓሲቭ ኮምፖኔንትስ)ን ብቻ ከያዘ መረብ ይወሳሰባል። ለዚህ ምክንያቱ ቀጥተኛ (ሊኒያር) ስላልሆኑና በቀላሉ የአልጀብራና የሽግግር መንገዶችን በኒህ ላይ መተግብር ስለማይቻል ነው።

የዑደት ትልም መንገድ (ኤሌክትሪካል ዲዛይን)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማናቸውንም የኤሌክትሪክ ዑደት ትልም (አናሎግ ኤሌክትሮኒክስም ሆነ ዲጂታል ኤሌክትሮኒክስ ለማቀነባበር የኤሌክትሪክ ኢንጂነሩ በያንዳንዷ የዑደቱ ነጥብ ላይ ሊኖር የሚችለውን የቮልቴጅ እና ጅረት መጠን በግልጽ ሊተነብይ ይገባል። በአንድ ዑደት ውስጥ ገቢውም ሆነው ወጭው የኤሌክትሪክ ድግግሞሽ የማይቀየር ከሆነ ያ የዑደት ሥርዓት ቀጥተኛ ዑደት (ሊኒያር ሰርኪዩት)ይባላል። እኒህ ወገን ዑደቶች የአቅጣጫ ቁጥርን በመጠቀም በእጅ ስሌት ሊሰሉና ሊተነተኑ ይችላሉ። ሌሎች ዑደቶች ጠባያቸውን በተመጣጣኝ ቀጥተኛ ዑደት በመተካት ወይንም ለዚህ ተግባር ተብሎ በተሰራ ሶፍትዌር፣ በኮምፒውተር ብቻ ሊተነተኑ ይገባል። ለዚህ ተግባር ተብለው ከተሰሩ ሶፍትዌሮች HSPICE ተጠቃሽነት ሲኖረው፣ ለትንተና ከተፈጠሩ የኤሌክትሪክ ሶፍትዌር ቋንቋወች VHDL-AMS እና verilog-AMS በኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክ ኢንጂኔሮች ዘንድ ታዋቂነት ካገኙ ወገኖች ናቸው።

የኤሌክትሪክ ህጎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለማናቸውም የኤሌክትሪክ መረቦች የሚሰሩ ጥቂት ናቸው የማይባሉ ህጎች በየዘመኑ ተገኝተዋል። ለምሳሌ ያልን እንደሆን፡

  • የኪርኮፍ ጅረት ህግ: አንድ ጉብር (ሽቦወች የሚገናኙበት ነጥብ) ውስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ጅረቶች መጠን ከዚያ ጉብር ከሚወጡ ጅረቶች መጠን ጋር እኩል ነው።
  • የኪርኮፍ ቮልቴጅ ህግ: አንድ ዙሮሽ ላይ ያለን አቅጣጫዊ የእምቅ አቅም ልዩነት (ቮልቴጅ) ብንደምር የምናገኘው ውጤት ዜሮ ነው።
  • የኦም ህግ፡ በአንድ የኤሌክትሪክ ተቃዋሚ ጫፎች መካከል ያለ የቮልቴጅ ልዩነት በተቃዋሚው ውስጥ የሚያልፈው ጅረት ሲባዛ በተቃዋሚው ዋጋ ነው።
  • የኖርተን እርጉጥ ማናቸውም የጅረትና ቮልቴጅ ምንጮችና የኤሌክትሪክ ተቃዋሚወች መረብ በአንድ የጅረት ምንጭና ለርሱ ትይዩ በተያያዘ አንድ ተቃዋሚ ሊተኩ ይችላሉ።
  • የቴቭኒን እርጉጥ: ማናቸውም የጅረትና ቮልቴጅ ምንጮሽና የኤሌክትሪክ ተቃዋሚወች መረብ በአንድ የቮልቴጅ ምንጭና ለርሱ በተቀጠለ አንድ ተቃዋሚ ለተኩ ይችላሉ።
  • ሰፊ ትግበራ ያላቸው መተንተኛዎች
  • ለሊኒያር መረብ ብቻ ለመተንተን የሚረዱ