Jump to content

ጉን

ከውክፔዲያ

ጉንቻይና አፈ ታሪክኋሥያ ንጉሥ ያው መኳንንት አንዱ ነበር። ከዚህ ቀድሞ በኋሥያ የነገሠው ዧንሡ የጉን ቅድመ-አያት መሆኑ ይባላል። ያው የቾንግ አገረ ገዥ አደረገው፤ ይህም ቦታ ደብረ ሶንግ እንደ ሆነ ይታመናል። በያው ዘመን የቻይና ታላቅ ጎርፍ በወንዞቹ ጀመረ። ስለዚህ ያው ጉንን ልዩ ሚኒስትር እንዲሆን ሾመው። ግድብ በመሥራት ወንዞቹን እንዲያስተዳድራቸው አዘዘው። ትውፊቶች እንድሚሉ፣ ግድብ ለመሥራት ልዩ ተዓምራዊ የአፈር አይነት «ሺራንግ» («ሕያው አፈር») ጠቀመው። ሆኖም ጉን ለ፱ ዓመታት ይህን ሞክሮ ጎርፎቹ እንደገና ግድቦቹን ሰበሩ፣ ብዙ መንደረኞች ተሰመጡ። ስለዚህ ያው ጉንን ሻረውና በፈንታው አማቹን ሹንን ሾመው። ከዚህ ጥቂት ጊዜ በኋላ ያው ዙፋኑን ትቶ ሹንንም አልጋ ወራሽ አድርጎት ያን ጊዜ ሹን የኋሥያ ንጉሥ ሆነ። ጉን ግን ወደ ዩሻን («የላባ ጠራራ») በስደት ሄደ። ሆኖም የጉን ልጅ ዩ ከዚህ በኋላ ጎርፎቹን በሺራንግ በመገድብ ተከናወነ፣ እርሱም የሹን ተከታይ ሆኖ «ዳ ዩ» («ታላቁ ዩ») ተብሎ የሥያ ስርወ መንግሥት የመሠረተ ነው።