Jump to content

የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ

ከውክፔዲያ
እስፊንክስ ከጎኑ ሲታይ
ፊት ከፊት ሲታይ

የጊዛ ታላቅ እስፊንክስጊዛ ሜዳ ግብጽ (ካይሮ አጠገብ) የሚገኝ ታላቅና ጥንታዊ ሐውልት ነው። የእስፊንክስ ቅርጽ የአንበሣ ገላ እና ሰብዓዊ ራስ አለው። ነገር ግን የቅሉ ቅርጽ እንደ ዘመናዊ ሰዎች አይሆንም። 2900 ዓክልበ. ዓመታት ገደማ በፈርዖን ካፍሬ ዘመን እንደ ተሠራ ይታመናል።

በመካከለኛው ዘመን ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ዘንድ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከማየ አይህ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች (የቃየልና የሴት ልጆች) ነበር ብለው ጻፉ።