ፊያኩ ቶልግራክ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ፊያኩ ቶልግራክአይርላንድ አፈታሪክ የነበረ ሰው ሲሆን ምናልባት የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር።

ከመካከለኛ ዘመን በሆኑት ምንጮች ዘንድ፣ ፍያካ ንጉሡን አርት ማክ ሉግዳክ ገደለው፣ በኋላም በተከታዩ አይሊል ፊን ዘመን ደግሞ (566-557 ዓክልበ. ግ. በድሮ አቆጣጠር)፣ ፍያካ በአይርጌትማር ወገን ላይ ውግያ ሲያደርግ ተገደለ፤ እንጂ ከፍተኛ ንጉሥ ከቶ አልሆነም።

በአንዳንድ ምንጭ ዘንድ በተለይ በ17ኛው ክፍለ ዘመን በወጡት ታሪኮች ዘንድ ግን፣ ፍያካ እራሱ ከአርት ማክ ሉግዳክ ቀጥሎና ከአይሊል ፊን በፊት ለ8 (ወይም 7 ወይም 10) ዓመታት ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘ፣ ከዚያ አይሊል ፊን ገደለው።