Jump to content

ፋሺዝም

ከውክፔዲያ

ፋሺዝም የፖለቲካዊ ርዕዮት ዓለም ሆኖ ሥልጣናዊነትን እና ጽንፈኛ ብሔርተኝነትን አዋህዶ የያዘ ነው። ከፋሽዝም መገለጫዎች ውስጥ፣ ፈላጭ ቆራጭነት፣ ተቃራኒ ሐሳቦችንም ሆነ ማሕበረሰቦች በፍጹም ማፈን፣ ኢኮኖሚውንና ማህበረሰቡን ደግሞ ዝንፍ በማይል ሥነ-ሥርዓት ማስተዳደር ይጠቀሳሉ። የፋሽዝም ኣባት እና ደራሲ የጣሊያኑ መሪ ቤኔቶ ሞሶሊኒ ነው።