ፍሪታውን

ከውክፔዲያ

ፍሪታውንሴራሊዮን ዋና ከተማ ነው።

ፍሪታውን ከሰማይ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1,051,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 08°30′ ሰሜን ኬክሮስ እና 13°17′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ቦታው መጀመርያ በ1779 ዓ.ም. በቀድሞ ባርያ ገበያ ሥፍራ ላይ በ400 ነጻ ጥቁሮች ከአሜሪካ ተሠፈረ። በአሜሪካ ነጻነት ጦርነት ጊዜ ለእንግሊዝ መንግሥት ታማኝ ስለ ነበሩ የእንግሊዝ ጸረ-ባርነት ድርጅቶች መሬት ለዋጋቸው ሰጣቸው። መሬቱን ከዙሪያው ተምኔ ወገን ገዙ። ነገር ግን ብዙዎቹ ሠፈረኞች ከበሽታ አርፈው ፍሪታውን በ1782 ዓ.ም. ተቃጠለ።

የሲዬራ ሊዎን ድርጅት (የእንግሊዝ ጸረ-ባርነት ድርጅት) እንደገና ሙከራ አድርጎ በ1784 ዓ.ም. 1,100 ነጻ ጥቁሮች ከአሜሪካ በፍሪታውን ተሠፈሩ። 500 ነጻ ሰዎች ከጃማይካም በ1792 ዓ.ም. ደረሱ። ከ1800 እስከ 1866 ዓ.ም. ድረስ የእንግሊዝ ምዕራብ አፍሪካ መቀመጫ ነበረ።