ፍርድ ቤት

ከውክፔዲያ
ፍርድ ቤት

ፍርድ ቤት ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የ መንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ ነው። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግአስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህልበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።

ገለልተኝነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገኝ ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።