ፔሪፓቶስ

ከውክፔዲያ
«የአሪስጣጣሊስ ትምህርት ቤት» በ1880 ዓም ገደማ እንደ ተሳለ።

ፔሪፓቶስአቴናግሪክ አገርአሪስጣጣሊስ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ከ343 እስከ 94 ዓክልበ. ድረስ ቆየ።

መገናኛ ቦታው በአረመኔ ጣኦት በአፖሎ ቤተ መቅደስ (ሊሲየም) ነበረ። አሪስጣጣሊስ ከ375 እስከ 355 ዓክልበ. በፕላቶ አካዳሚ አባል ነበረ፣ ከዚያ የራሱን ትምህርት ቤት በሊሲየም ጀመረ።

እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስተማሪና ተማሮች ተለይተው ሳይሆን፣ እንደ አካዳሚ ግን ከፍተኛ እና ታቸኛ አባላት ነበሩ። ትምህርቱ በጥያቄና መልስ ይካሄድ ነበር። በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ፍልስፍናየተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትና ሌላ የታወቀ ሳይንስ ዕውቀት ነበሩ።

አሪስጣጣሊስ በ330 አክልበ. አረፈና እስከ 296 ዓክልበ. ድረስ የነበሩት አስተዳዳሪዎች ከአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና በላይ ምንም ይፋዊ ርዕዮተ አለም አላስተማሩም። ይህም ማናቸውንም ፍልስፍና ወይም ዕውቀት ለመሰብሰብ ነበረ።

በ296-277 ዓክልበ. የተቋሙ ሦስተኛ መሪ የሆነው ስትራቶ ዘላምፕሳኮስ ያስተማረው ርዕዮተ አለም የአምላክ ሚና የሚክድ ሲሆን ይህ ትምህርት የከሃዲነት መንስኤ ሆነ።

በ94 ዓክልበ. የሮሜ መንግሥት አለቃ ሱላ ከተማውን በሠራዊት ይዞ ተቋሙን አጠፋ። የአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና ወገን ከዚህ በኋላ አነስተኛ ቢሆንም ለጊዜ ተለይቶ ቀረ፣ ከፕሎቲኖስ (197-262 ዓም የኖረ ፈላስፋ) በኋላ ግን «አዲስ ፕላቶኒስት» የተባለው ፍልስፍና ተነሥቶ በርቶ የአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና በእርሱ ውስጥ ተጨመረ። የአሪስጣጣሊስ ትምህርቶችና ጽሑፎች በተለይ በእስልምና ፍልስፍና ውስጥ ተጽእኖ ነበራቸው፣ በአውሮፓ ክርስትና አለም ግን እስከ 1200 ዓም ድረስ ተረስተው ነበር።