የጥንት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
Appearance
በጥንታዊ ቻይና ከአፈታሪካዊ ዘመን ነገሥታት ጀምሮ (ምናልባት 2350 ዓክልበ.) በቤተመንግሥታቸው ቸንግ ጁ የተባለ ተቋም እንደ መሠረቱ ይባላል፤ ይህም በልዩ ልዩ ዋና ከተሞችና በልዩ ልዩ ስሞች እስከ 229 ዓክልበ. ድረስ ቆየ። ያስተማሩት ጥናቶች ቀስትን ማስፍንጠር፣ ሠረገላን መንዳት፣ ሙዚቃ፣ ጽሕፈት፣ ሥነ ቁጥር፣ ሥነ ፈለክ ጠቀለሉ።
እንዲሁም በአውሮፓ አፈ ታሪክ የኬልቲካ (የአሁን ፈረንሳይ) ነገሥታት ከ2200 ዓክልበ. ግድም ከፍተኛ ተቋማት ለድሩዊዶች እንደ ነበሯቸው ተጽፏል። ለነዚህ ግን ምንም ማስረጃ ቅርስ አልተገኘም። በተጨማሪ ከጥንታዊ ግብጽ ዘመን (3000 ዓክልበ. ያህል) ጀምሮና በብዙ ጥንታዊ አገራት፣ በቤተ መንግሥታቸው ወይም በቤተ መቅደሳቸው ዙሪያ የመጻሕፍት ቤትና ጽሕፈትን ወዘተ. የተማሩ መምህሮች ነበሩዋቸው። ለምሳሌ፣ የአይሁድና መጻሕፍት በንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አጠገብ ተገኙ።
ከ1200 ዓም አስቀድሞ የተመሠረቱት ዋና ታዋቂ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እነዚህ ናቸው፦
- ታክሲላ - በአሁኑ ፓኪስታን፤ ምናልባት ከ600 ዓክልበ. እስከ 460 ዓም ያህል ቆየ። (የቡዲስም ተቋም)
- የፕላቶ አካዳሚ - በአቴና፣ ግሪክ አገር በፕላቶ ተመሠረተ። ከ395 እስከ 94 ዓክልበ. እና እንደገና ከ402-521 ዓም ቆየ።
- ፔሪፓቶስ - በአቴና፣ ግሪክ በአሪስጣጣሊስ ተመሠረተ። ከ343 እስከ 94 ዓክልበ. ቆየ።
- ሙሴዎን - በእስክንድርያ ግብጽ፤ ከ300 ዓክልበ. ግድም እስከ 264 ዓም ቆየ።
- ፑርሽፐጊሪ ቪሃረ - በኦዲሻ፣ ሕንድ፤ 250 ዓክልበ.-1200 ዓም ግድም። (~1,450 ዓመት፣ ቡዲስት ገዳም)
- አኑራደፑረ መሃቪሃረ - በስሪ ላንካ፣ 244 ዓክልበ.-አሁን ቆየ (2,254 ዓመት፣ ቡዲስት ገዳም)
- አበየጊሪ ቪሃረ - ስሪ ላንካ፣ 80 ዓክልበ. - 1157 ዓም. (1,237 ዓመት፣ ቡዲስት ገዳም)
- ታይሥዌ - ቻይና በተለያዩት ዋና ከተሞች፤ 6 ዓክልበ. - 573 ዓም፣ ስሙ ጐዝርጅየን ሆነ 573-1897 ዓም (1,903 ዓመት ቆመ፣ ኮንግ-ፉጸ ተቋም)
- የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት - ግብጽ፣ 54-383 ዓም (ክርስትና ተቋም)
- ቪጃየፑሪ - በሕንድ 90-340 ዓም ግድም (ቡዲስት ገዳም)
- የአንጾኪያ ማስተማርያ ቤት 170-460 ዓም ግድም (ክርስትና ተቋም)
- ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ - ቻይና 250 ዓም-አሁን (እንደ «ናንጂንግ ታይሥዌ» ኮንግ-ፉጸ ተቋም ተመሠረተ፣ 1,760 ዓመት)
- ጄተቨነራመየ - ስሪ ላንካ፣ 270-1157 ዓም (ቡዲስት ገዳም)
- የኒሲቢስ ትምህርት ቤት - አሁን ቱርክ፣ 342-824 ዓም (ኔስቶራዊ ክርስትና ተቋም) (356-480 ዓም የኤደሣ ትምህርት ቤት ነበር።)
- ታይሃክ - ኮርያ፣ 364 ዓም - አሁን፤ በልዩ ልዩ ስሞች፣ አሁን ሱንግክዩንኳን ዩኒቨርሲቲ ይባላል ( 1,635 ዓመት)።
- ፓንዲዳክቴሪዮን - በቁስጥንጥንያ፣ 417-1445 ዓም (1,028 ዓመት) ቆየ። (ክርስትና ተቋም)
- ናለንዳ -በቢሓር፣ ሕንድ፤ 440-1200 ዓም ግድም። (ቡዲስት ገዳም)
- ኦዳንታፑሪ - በቢሓር፣ ሕንድ፤ 540-1030 ዓም ግድም። (ቡዲስት ገዳም)
- ጎንደሻፑር አካዳሚ - ፋርስ፣ 550-900 ዓም ግድም (ኔስቶራዊ ክርስትና ተቋም)
- ቫላቢ - ጉጃራት፣ ሕንድ፣ 600-1200 ዓም ግድም። (ቡዲስት ተቋም)
- ሻረዳ ፒጥ - በአሁኑ ፓኪስታን፣ 600-1330 ዓም ግድም። (የሂንዱኢዝም ተቋም)
- ዳይጋኩርዮ - ጃፓን - 663-1169 ዓም ቆየ። (ኮንግ-ፉጸ ተቋም)
- ሶማፑራ - በአሁኑ ባንግላዴሽ 800-1170 ዓም ግድም። (ቡዲስት ገዳም)
- ቪክረመሺላ - ሕንድ፣ 800-1200 ዓም ግድም (ቡዲስት ገዳም)
- ቤተ ጥበብ - ባግዳድ፣ 824-1250 ዓም (እስልምና ተቋም)
- አል-ቃራዊዪን ዩኒቨርስቲ - ሞሮኮ፣ 851-አሁን (እስልምና ተቋም፣ 1,159 ዓመት)
- የፕረስላቭ ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ቤት - ቡልጋሪያ፣ 878-964 ዓም (የክርስትና ተቋም)
- አሺካጋ ጋኮ - ጃፓን፣ 900-1860 ዓም ግድም (ኮንግ-ፉጸ ተቋም፣ 960 ዓመት)
- ነጭ አጋዘን ዋሻ - ቻይና፣ 929-1600 ዓም ግድም (ኮንግ-ፉጸ ተቋም)
- አል-አዣር ዩኒቨርስቲ - ግብጽ፣ 964 ዓም-አሁን (እስልምና ተቋም፣ 1,057 ዓመት)
- ዩዌሉ አካዳሚ - ቻይና፣ 968-1895 ዓም (ኮንግ-ፉጸ ተቋም 927 ዓመት)
- ሳንኮሬ ማድራሣ - ቲምቡክቱ፣ ማሊ፣ 981-1585 ዓም (እስልምና ተቋም)
- ቤተ ዕውቀት - ግብጽ፣ 991-1163 ዓም (የእስልምና ተቋም)
- የባግዳድ ኒዛሚያ - ባግዳድ፣ ኢራቅ፣ 1057-1250 ዓም (የእስልምና ተቋም)
- ኰክ ቲ ግየም - ቬትናም፣ 1068-1771 ዓም (ኮንግ-ፉጸ ተቋም)
- የቦሎኛ ዩኒቨርሲቲ - ጣልያን፣ 1080 ዓም-አሁን (የዓለም መጀመርያ «ዘመናዊ» ዩኒቨርስቲ በመሆኑ ይኮራል። 930 ዓመት)
- ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኦክስፎርድ - እንግላንድ፣ 1088-አሁን 922 ዓመት
- ጃገዳላ - በአሁኑ ባንግላዴሽ፣ 1100-1200 ዓም ግድም። (ቡዲስት ገዳም)
- ዶንግሊን አካዳሚ - ቻይና፣ 1103-1618 ዓም (ኮንግ-ፉጸ ተቋም)
- የሳላማንካ ዩኒቨርሲቲ - ስፔን፣ 1126-አሁን