Jump to content

ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ

ከውክፔዲያ
አዳራሽ

ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ (ቻይንኛ፦ 南京大学 /ናንጂንግ ዳሥዌ/) በናንጂንግቻይና የሚገኝ ጥንታዊ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው።

መጀመርያው በ250 ዓም ናንጂንግ ታይሥዌ ተብሎ እንደ ኮንግ-ፉጸ ተቋም ተመሠረተ፣ ስለዚህ ለ1,760 ዓመት ክፍት ሆኗል። ይህ ከ571 ዓም በኋላ ናንጂንግ ዋና ከተማ በሆነባቸው ጊዜዎች ናንጂንግ ጐዝርጅየን ሆነ። ዋና ከተማ ባልሆነባቸው ጊዜዎች ደግሞ ናንጂንግ ሹዩዋን (ናንጂንግ አካዳሚ) ይባል ነበር።

1894 ዓም ናንጂንግ ሹዩዋን «ዘመናዊ» ትምህርት ቤት (በጃፓናዊ አራያ) ተደረገ። ከዚያ ጀምሮ የሚከተሉት ስያሜዎች ነበሩት፦ ሳንጅየንግ ልምዳዊ ኮሌጅ (1894 ዓም)፣ ልየንግጅየን ልምዳዊ ኮሌጅ (1898 ዓም)፣ ናንጁንግ ከፍተኛ ልምዳዊ ትምህርት ቤት (1907 ዓም)፤ ብሔራዊ ደቡብ-ምሥራቃዊ ዩኒቨርሲቲ (1913 ዓም)፣ ብሔራዊ ናንጂንግ ቹንግሻን ዩኒቨርሲቲ (1919 ዓም)፣ ጅየንግሱ ዩኒቨርሲቲብሔራዊ መካከለኛ ዩኒቨርሲቲ (1920 ዓም)፣ ብሔራዊ ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ (1941 ዓም)፣ በመጨረሻም ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ (1942 ዓም)።

መጀመርያው ተቋም «የኮን-ፉጸ ስድስቱ ሞያዎች» አስተማረ። 1) የኮንግፉጸ ሥርአተ ቅዳሴ፣ 2) የቻይና ባህላዊ ሙዚቃ፣ 3) ቀስትን ማስፈንጠር፣ 4) ሰረገላ መንዳት፣ 5) የቁም ጽሕፈት፣ 6) ሥነ ቁጥር ነበሩ።

በ462 ዓም ጥናቶቹም፦ 1) ሥነ ጽሑፍ፣ 2) ታሪክ፣ 3) የኮንግ-ፉጸ ትምህርት፣ ፬) የዳዊስም ትምህርት፣ ፭) የዪንግ-ያንግ ጥናት (የተፈጥሮ ጥናት) ነበሩ።

በዚያ ዘመን ታዋቂ ከሆኑት ተማሮችና መምህሮች መካከል፦

በ1373 ዓም 10,000 ተማሮች ነበሩ። ጥናቶቹም፦ የኮንግ-ፉጸ ስነ ጽሑፍ፣ ታሪክ፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ሥነ ቁጥር፣ ሕግ፣ የቁም ጽሕፈት፣ ፈረሰኝነት፣ ቀስትን ማስፈንጠር፣ ወዘተርፈ. ነበሩ። ተቋሙ በ1400 ዓም ዮንግሌ መዝገበ ዕውቀት አሳተመ።

በዚሁ ዘመን ተማሮች ነበሩ።

በ1913 ዓም የነበሩት ክፍሎች፦ ሥነ ጥበብትምህርትግብርናምህንድስናንግድ ነበሩ። ዛሬም በጣም ብዙ ዘርፎች ሲኖሩ ከአገሩ ፪ኛው ዋና ዩኒቨርሲቲ ነው። በኬሚስትሪ ዘርፍ ደግሞ በክቡርነት ከአለም ፫ኛ ነው። 14,000 ያህል ተማሮች አሉበት።