ፖዶስክ

ከውክፔዲያ
የ ፖዶስክ ከተማ

Подольск (መስኮብኛ)

Holy Trinity Church Podolsk 2.jpg
ክፍለ ሃገር መስኮብ ኦብላስት
ዋና ከተማ ፖዶስክ
Flag of Podolsk (Moscow oblast).svg Coat of Arms of Podolsk (Moscow oblast).png
የፖዶስክ ሰንደቅ ዓላማ የፖዶስክ አርማ
Map of Russia - Moscow Oblast (2008-03).svg
ሊቀ መንበር ኒኮላይ ፔስቶቭ
የመሬት ስፋት 37.92ካሬ ኪ.ሜ.
የህዝብ ብዛት (2005) 179,974
ሰዓት_ክልል +7

ፓዶስክ (በመስኮብኛ Подо́льск)ሩሲያ የምትገኝ የሞስኮ ኦብላስት ክፍለ ሃገር አውራጃ የሆነቸው ፖዶስኪ ግዛት ዋና ከተማ ናት። ከሞስኮ ኦብላስት ከተማወች ሁሉ ታላቋ ስትሆን በከተማይቱ 179 ሺህ በላይ ህዝብ አሁን ይኖራል።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፖዶስክ ከተማ የተቆረቆረው ድሮ ፖዶል ተብሎ ከሚታወቅ መንደር ሲሆን እስከ 18ኛው ክፍለዘመን መገባደጃ ሞስኮ ይገኝ የነበረው ዳኒሎቭ ደብር ርስት ነበር። በ1791 የሩሲያዋ ዳግማዊ ካትሪን አዳዲስ ከተሞችንና ክፍለ ሃገሮችን በአጠቃላይ ሩሲያ በምትፈጥርበትና አስተዳዳሪወችን በምትሾምበት ወቅት ፖዶስክን በከተማ ደረጃ እውቅና ሰጠች።

ከ1917ቱ የሩሲያ አብዮት በፊት ፖድስክ በኢንደስትሪ ከበለጸጉ የሩሲያ ከተሞች ቀደምት ተርታ ነበር። የልብስ ስፌት ማሽን የሚያመርተው ሲንገር ፋብሪካ በዚሁ ወቅት በከተማው ተሰማርቶ ነበር።

በ ሶሺያሊዝም (ሶቪየት) ዘመን ፖዶስክ እንዲሁ የከባድ ኢንድስትሪወች ማዕከል ነበር። ወደ 70 የሚጠጉ ኢንደስትሪወች በከተማው የነበሩ ሲሆን አብላጫው የከተማዋ ነዋሪ በኒሁ ኢንደርስትሪወች በመቀጠረ ኑሮውን ይመራ ነበር።

በ1992ዓ.ም. ታላቅ የጦር ሰራዊት ሰፈር ከከተማዋ .07 miles ርቆ የተመሰረተ ሲሆን የሚመራውም በኢጎር ሚኒን ነው። የ[ሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ማዕከላዊ ቤተ መዛግብት]] የሚገኘውም በዚሁ በፖድስክ ነው።