3 ሻምሺ-አዳድ

ከውክፔዲያ

3 ሻምሺ-አዳድአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ16 ዓመታት (ከ1539 እስከ 1524 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ።

ቀዳሚው የ2 እሽመ-ዳጋን ልጅ ሲሆን እርሱ ግን የሌላ እሽመ-ዳጋን (የሹ-ኒኑዓ ልጅ የሆነ) ልጅ እንደ ነበር ይላል። ለዚሁ ንጉሥ አንዳንድ ጥቃቅን ቅርሶች በአሹር ተገኝተዋል፤ ሆኖም ከዚህ ዘመን ምንም ሌላ መረጃ የለም። ተከታዩ ወንድሙ 1 አሹር-ኒራሪ ነበር።

ቀዳሚው
2 እሽመ-ዳጋን
የአሦር ንጉሥ
1539-1524 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 አሹር-ኒራሪ