ጉብር ትንታኔ
ሊኒያር መረብ ትንታኔ | |
---|---|
አባላት | |
አካላት | |
ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች | |
ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ | |
ተመጣጣኝ እርግጦች | የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች |
መረብ መተንተኛ ዘዴዎች | |
ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ | |
ጉብር ትንታኔ የኤሌክትሪክ ዑደትን ለመተንተን እና በእያንዳንዱ የኤሌክትሪክ ጉብር (መጋጠሚያ ነጥብ) ላይ ያለን የኤሌክትሪክ እምቅ አቅምን ለማስላት የሚረዳ የሥነ ኤሌክትሪክ መሰረታዊ መሳሪያ ነው። በሌላ አነጋገር፣ ጉብር ትንታኔ የአንድ ኤሌክትሪክ ዑደት ቅርንጫፍ ጅረትንና ቅርንጫፍ ቮልቴጅ በመጠቀም የዚያን ነጥብ ቮልቴጅ ከአንድ በነሲብ የተመረጠ ጉብር አንጻር የምናሰላበት ዋና መሳሪያ ነው።
1. የኤሌክትሪክ ዑደቱ ሽቦዎች እሚጋጠሙባቸውን ነጥቦች በሙሉ ንቅሰህ አውጣ። እኒህ መጋጠሚያዎች ጉብር (ኖድ) ይባላሉ።
2. ከነዚህ ጉብሮች አንዱን በነሲብ መርጠህ ዋቢ ጉብር (ማነጻጸሪያ ጉብር) አድርግ።
- የዋቢ ጉብሩ ማናቸውም ነጥቦች ሊሆን ይችላል። ለመስሉ ለውጥ አያመጣም። ሆኖም ብዙ ሽቦዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተገናኙትን ጉብር መምረጥ ትንታኔውን ያቃልላል።
3. ቮልቴጃቸው የማይታዎቁቱን ሁሉን ጉብሮች ስም ስጥ። ቮልቴጁ እሚታዎቀውን ጉብር መሰየም አስፈላጊ አይደለም።
4. ለእያንዳንዱ የማይታዎቅ የጉብር ቮልቴጅ ፣ የኪርኮፍ ጅረት ህግን በመጠቀም የጅረት ፍሰቱን እኩልዮሽ ጻፍ።
5. በሁለት ቮልቴጃቸው የማይታወቁ ጉብሮች መካከል የቮልቴጅ ምንጭ ካለ፣ ሁለቱን ጉብሮች አንድ ላይ በመጭመቅ ሱፐር ጉብር ፍጠር። የሁለቱ ጉብሮች ጅረት በአንድ እኩልዮሽ ይጠቃለልና አዲስ የቮልቴጅ እኩልዮሽ ይጻፋል።
6. ከኒህ ደረጃዎች በኋላ የሚፈጠረውን የሳይመልታኒየስ እኩልዮሽ ስርዓት፣ በሒሳብ ፈተህ፣ የጉብሮቹን ቮልቴጅ አግኝ።
በዚህ ዑደት ያልታወቀው ቮልቴጅ V1 ብቻ ነው። በዚህ ዑደት ሦሥት ግንኙነቶች ሲኖሩ፣ ሦስት ጅረቶች ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው። የነዚህ ጅረቶች አቅጣጫ ከጉብሩ ወጥተው እንደሚፈሱ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በመነሳት
- በተቃዋሚ R1 የሚፈሰው ጅረት እንዲህ ይሰላል: (V1 - VS) / R1
- በተቃዋሚ R2 የሚፈሰው ጅረት እንዲህ ይሰላል: V1 / R2
- በጅረት ምንጭ IS ውስጥ የሚፈሰው ጅረት ደግሞ: -IS ነው
የኪርኮፍ ጅረት ህግን በተጠቀሰው ጉብር ላይ ስንተገብር:
ይህን እኩልዮች ከ V1 አንጻር ስንፈታ:
ለተጠቀሱት ተለዋዋጮች የተሰጡትን የቁጥር ዋጋዎች ከላይ ባገኘነው እኩልዮሽ ስንተካ ውጤቱ እንዲህ ይሆናል