ግሸን ተራራ
Appearance
ግሸን ተራራ በአሁኑ ደቡብ ወሎ የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ተራራ ነው። የታሪካዊነቱ ምንጭ የዕርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ሲባል እንደ ደብረ ዳሞ (ትግራይ) እና ወህኒ (ጎንደር) የነገስታት ወንድ ተገዳዳሪ ዝርያወች በአምባው ላይ ይታሰሩ ስለነበር ነው። አጼ ጅን አሰገድ ወንድሞቻቸውንና ወንድ ልጆቻቸውን በአምባ ግሸን እንዳሳሰሩ በዜና መዋዕላቸው ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ሆኖም ግን ይህን ስራ እኒህ ንጉስ ያስጀምሩት ወይም ከሳቸው በፊት ይጀመር በታሪክ ተመዝግቦ የተገኘ እርግጠኛ ማስታወሻ የለም። በዚህ አምባ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ወንድ የነገስታት ዘሮችን ያሳሰሩ ንጉስ አጼ ናዖድ ነበሩ። በፖርቱጊዝ ተጓዦች ምክንያት ተራራው በጥንቶቹ አውሮጳውያን ዘንድ ታዋቂነትን አትርፎ ነበር። የዚህ ዘመን አውሮጳወች በግሸን ሳይሆን አምባ አማራ በማለት ያውቁት ነበር። ጆህን ሚልተን የተሰኘው የእንግሊዙ ታዋቂ ገጣሚ ይህ በርግጥም የጠፋው የገነት ተራራ ነው በሚል አስተሳሰብ በ1664 ስለተራራው እንዲህ ሲል ገጥሟል፦
- Nor where Abassin Kings thir issue Guard,
- Mount Amara, though this by som suppos'd
- True Paradise under the Ethiop Line
- By Nilus head, enclosd with shining Rock,
- A whole days journy high, but wide remote [1]
ሌላው ታዋቂው የእንግሊዝ ደራሲ ኮልሪጅ እንዲሁ ስለዚህ ተራራ ገጥሟል። አህመድ ግራኝ አምባውን ለመያዝ ሁለት ጊዜ ሞክሮ ሳይሳካለት በሶስተኛው ግን በመቻሉ የተራራውን ኗሪወች በሙሉ እንደገደለ ዜና መዋዕሉ ያትታል።
-
ግሸን ቤተክርስቲያን
-
ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የሚያሻግረው ብቸኛው መንገድ]]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ John Milton, Paradise Lost BOOK 4፣ 1664