Jump to content

ሻርላግ

ከውክፔዲያ
የ14:03, 21 ጁን 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ሻርላግአካድ ንጉሥ ሻርካሊሻሪ ዘመን የጉታውያን ንጉሥ ነበረ። ይህ የሚታወቀው ከሻርካሊሻሪ የዓመት ስም፣ «ሻርካሊሻሪ የጣኦታት ቤተ መቅደስ በባቢሎን ሠርቶ የጉቲዩም ንጉሥ ሻርላግን የማረከበት ዓመት» ነው። ይህ ዓመት ምናልባት 2020 ዓክልበ. አካባቢ ነበር (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር)።

ሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ደግሞ ከጉታውያን ከተዘረዘሩት ነገሥታት የ፪ኛው ስም «ዛርላጋብ» ወይም «ሳርላጋብ» ሲሆን ለ፮ ዓመታት ንጉሥነቱን እንደያዘ ይላል። በአንድ አስተሳሰብ ዘንድ ይህ ሳርላጋብ ምናልባት በሻርካሊሻሪ ዘመን የተማረከው ሻርላግ ይሆናል።