መርሰኸምሬ
Appearance
==
መርሰኸምሬ | |
---|---|
«መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» የሚል አንዱ ሐውልት | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1656-1653 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰዋጅተው |
ተከታይ | ሰውጅካሬ ሆሪ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
መርሰኸምሬ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1656 እስከ 1653 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ስሙ መርሰኸምሬ የታወቀው ከሦስት ምንጮች ነው፦
- በቶሪኖ ቀኖና ሰነድ፣ ከሰዋጅተው ቀጥሎ «መርሰኸምሬ ኢነድ» ተዘረዘረ። ሦስት አመት፣ አንድ ወርና አንድ ቀን እንደ ነገሠ ይላል።
- በካርናክ ዝርዝርም ላይ አንድ «መርሰኸምሬ» ይገኛል፣ ይህ ዝርዝር ግን ቅድመ-ተከተል አይጠብቅም።
- ሁለት «መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» የሚሉ ሐውልቶች በሥነ ቅርስ ከካርናክ ተገኝተዋል።
ብዙ ሊቃውንት እንደሚሉ፣ ሁላቸው አንድ ነውና የመርሰኸምሬ ሌሎች ስሞች ኢነድና ነፈርሆተፕ ናቸው። አንዳንድ መምህር ግን «መርሰኸምሬ ኢነድ»ና «መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» ልዩ ልዩ ፈርዖኖች ነበሩ ብለው ያምናሉ።
በዚሁ ዘመን የሥርወ መንግሥቱ ሥልጣን ከጤቤስ ከተማ በጣም እንዳልራቀ፣ ሂክሶስም ወገኖች በስሜን እንደ ገዙ ይታስባል።
ቀዳሚው ሰዋጅተው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1656-1653 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሰውጅካሬ ሆሪ |
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)