Jump to content

3 ፑዙር-አሹር

ከውክፔዲያ
የ17:10, 27 ኖቬምበር 2018 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

3 ፑዙር-አሹርአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ 24 ዓመታት (ከ1499 እስከ 1476 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ።

ቀዳሚው 1 አሹር-ኒራሪ አባቱ ነበር። ። በአሹር (አሦር) ከተማ አንዳንድ አረመኔ ቤተ መቅደስ እንዳሳደሰ ይታወቃል።

«የወቅቶች ሥመራ ዜና መዋዕል» (ABC 21) በተባለው ጽላት ይጠቀሳል፦

«የአሦር ንጉሥ ፑዙር-አሹርና የካርዱኒያሽ (የካሣውያን ባቢሎን ግዛት) ንጉሥ ቡርና-ቡርያሽ (1483-1473 ዓክልበ. ገደማ) መሓላ ገብተው ይህኑንም ድንበር ወስነው ተስማሙ።»
ቀዳሚው
1 አሹር-ኒራሪ
የአሦር ንጉሥ
1499-1476 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ኤንሊል-ናሲር