Jump to content

ቡታጅራ

ከውክፔዲያ
የ02:41, 8 ሜይ 2019 ዕትም (ከPlyrStar93 (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ቡታጅራደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና የጉራጌ ዞን ከተማና ልዩ ወረዳ ነው። በመስቃን ወረዳ ይከበባል።

ቡታጅራ የመብራት ኃይል፣ የስልክና የፖስታ ቤት አገልግሎት ካሉዋቸው ከተሞች አንዱ ነው። የብታጅራ ገበያ በየዓርቡ ይካሄዳል።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተቀደሠ ምንጭ አለ፤ የከተማ መስጊድ ደግሞ በ1972 ዓም ተሠራ።

በ1918 ዓም ሚስዮኑ ፔር አዛዕዝ በሥፍራው ምንም አላገኘም። በ1927 ዓም ግን አንድ ጀርመናዊ ጉዞ ከተማው የጉራጌ አገር መቀመጫ ሆኖ እንደ ተመሠረተ አመለከተ። በ1929 ዓም ጣልያኖቹ ራስ ደስታ ዳምጠውን በቡታጅራ ገደሉዋቸው። በ1933 ዓም አርበኞችና የብሪታንያ ጭፍሮችም ከተማውን ነጻ አወጡት።

የሕዝብ ቁጥር በ1999 ዓም በ33,406 ሰዎች ተቆጠረ።