ወፍ
Appearance
ወፎች ወይም አዕዋፍ ክንፍ ያላቸው፣ ደመ ሞቃት፣ የጀርባ አጥንት ያላቸው እና እንቁላል ጣይ የሆኑ የእንስሳት መደብ አባላት ናቸው። በምድራችን ላይ ከ10,000 በላይ የወፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። በዚህም ወፎች በአለማችን ብዙ ዝርያ ያላቸው ባለጀርባ አጥንት እንስሳት ያደርጋቸዋል። ወፎች ከመሬት ላይኛው ጫፍ (አርክቲክ) እስከ ደቡባዊ ጫፍ (አንታርክቲካ) ድረስ ባላው ቦታ ይኖራሉ። መጠናቸው ከ5 ሣ.ሜ. (ሁለት ኢንች) የምትረዝመው ትንሿ ወፍ እስከ 3 ሜትር (አስር ጫማ) የምትረዝመው ሰጎን ድረስ ይለያያል።
ዳክዬ በአብዛኛው በጨዋማና በለጋ ውሃ ላይ የሚኖር የወፍ ዘር ነው። ዳክዬ በአማካኝ 6ኪሎ ይመዝናል።