Jump to content

የሲና ልሳነ ምድር

ከውክፔዲያ
የ16:36, 25 ኖቬምበር 2022 ዕትም (ከGerd Eichmann (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የሲና ልሳነ ምድር ከጠፈር ታይቶ

የሲና ልሳነ ምድርግብጽ የሚገኝ ሲሆን የእስያ አሕጉር ክፍል ይቆጠራል። ከአፍሪካና ከእስያ መካከል የሚሆን የመሬት ድልድይ ነው፣ እንዲሁም ከሜዲቴራኔያን ባህርና ከቀይ ባህር መካከል ነው። እነዚህም ባህሮች በስዌዝ ቦይ ይቀጣጠላሉ።

የሲና ልሳነ ምድር ከምሥራቁ ታስይቶ

ጥንታዊ ግብጽ ፈርዖኖች ከ1ኛው ስርወ መንግሥት ጀምሮ ወደ ሲና ለማዕድን በተለይም ለበሉር ለማግኘት ጉዞዎች ያካሂዱ ነበር። በልሳነ ምድሩም የሚገኘው ደብረ ሲናመጽሐፈ ሄኖክ ይጠቀሳል፣ እንዲሁም በኦሪት መሠረት ሙሴ ሕገ ሙሴን የተሰጠበት ቅዱስ ቦታ ነው።