Jump to content

ዴቪድ ሊቪንግስተን

ከውክፔዲያ
(ከDavid livingston የተዛወረ)
ዴቪድ ሊቪንግስተን

ዴቪድ ሊቪንግስተን፣ ታዋቂ ሀገር አሳሽ፣ በ19 ማርች 1813 እ.ኤ.አ. ከአባታቸው ኒል ሊቪንግስተን እና ከእናታቸው ወይዘሮ አግነስ በታላቅዋ ብሪታንያ ግዛት ስኮትላንድ ተወለዱ። በህክምና ሚሲዮንነቱ ታዋቂ የነበረወን የለንደን ሚሲዮናዊ ማህበር ተቀላቅለው በዲሴምበር 1840 እ.ኤ.አ. ለኩሩማን በአሁኑዋ ደቡብ አፍሪካ መርከብ ተሳፈሩ። በዳሰሳቸውም በዚምባብዌ እና በዛምቢያ ድንበር ላይ የሚገኘውን ሞሲ ኦዋ ቱንያ ወይንም በተለምዶው ቪክቶሪያ ፏፏቴን የጎበኙ የመጀመሪያው አውሮፓዊ ሆነዋል። በዳሰሳ ላይ ሳሉ ለአመታት ሲያሰቃያቸው የነበረው የወባ አና ተቅማጥ በሽታ በሜይ 1 1873 እ.ኤ.አ. በዛምብያ ሃገር ለህልፍተ ህይወት በቁ።