Jump to content

መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ከውክፔዲያ
መቀሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ከፍታ 2257 ሜትር
መቀሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
መቀሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ

13°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°53′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ ከመቀሌ በአሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ዘመናዊ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ነው።

አየር ማረፊያው በዘመናዊ መልክ የተገነባ እና የተደራጀ ሲሆን ከባሕር ወለል በ ፪ሺ ፪መቶ ፶፯ ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ባሁኑ ጊዜ አየር ማረፊያው አንድ ባለ ፫ሺ ፮፻ ሜትር ርዝመት በ፵፫ ሜትር ስፋት ያለው አስፋልት የለበሰ ማኮብኮቢያ ያለው ሲሆን እንደ ቦይንግ ፯መቶ ፶፯ አይነት አየር ዠበቦችን ማስተናገድ ይችላል። ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉት እንደ ጉምሩክኢሚግሬሽን፣ የደህንነት ተቋማትና ኳራንቲን የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ያሟላ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሕር-ዳርን እና መቀሌን ከካርቱም ጋር በማገናኘት ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ዓለም አቀፍ በረራ የጀመረ ሲሆን፣ የሁለቱን አገራት የንግድ፤ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር የላቀ ሚና እንደሚኖረው ይገመታል። የበረራ መስመሩ በሳምንት ለአራት ቀናት የሚከናወን ሲሆን፣ ሰሜን ሱዳንን ከሰሜን የአገራችን ክፍል በቀጥታ የሚያገናኝ ነው። አየር መንገዱ ከሱዳን ለሚመጡ ጎብኝዎች የአባይ ወንዝን ምንጭ፤ የጢስ እሳት ፏፏቴን፤ በ፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገነባውን እና በአፍሪቃ የመጀመሪያው መስጊድ እንደሆነ የሚነገርለትን አል ነጃሺ መስጊድ እና ሌሎችንም የሰሜን ኢትዮጵያ መስህቦዎችን ለመጎብኘት እንደሚያመቻች ይታመናል።

ከዚህ በተጨማሪም መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቅርቡ ያስገባውን፣ ፻፶ ቶን ማስተናገድ የሚችል ቀዝቃዛ መጋዘን በመጠቀም የአበባፍራፍሬአታክልትዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን በቀጥታ ወደዓለም ገበያዎች ማጓጓዝ በቅርቡ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ አድርጓል።