Jump to content

ሴቪንግ አካውንት

ከውክፔዲያ
(ከሴቪንግ የተዛወረ)

ሴቪንግ አካውንት ገንዘብን ለአጭር ጊዜ(ከ1-5 ዓመት) ለመቆጠብ ከሚያስችሉት ሁለት የባንክ ቤት ግልጋሎቶች አንዱ ነው። ሌላኛው የአጭር ጊዜ ቁጠባ መንገድ ሲዲ ወይንም ሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚት ይሰኛል።

ሴቪንግ አካውንት ገንዘብን በቀላሉ ለማጠራቀምና እንዲሁም ለማውጣት ይረዳል። የማስቀመጥና የማውጣት ሂደትን ለመከታተል የሚረዳ ፓስ ቡክ ወይንም ባንክ ቡክ የሚባል ዶሴ ባንኮች ለደንበኞቻቸው ይሰጣሉ።

የሴቪንግ አካውንት ጥቅም የተጠራቀመን ገንዘብ በቀላሉ ማውጣትና ማስገባት ማስቻሉ፣ እንዲሁም ለተቀመጠ ገንዘብ ወለድ መስጤቱ ነው። የዚህ ወለድ መንስዔ ደንበኛ ያስቀመጠውን ገንዘብ ባንኮች ለሌላ ደንበኛ በማበደር ወለድ ስለሚያገኙበት ነው። ስለሆነም በሴቪንግ አካውንት ውስጥ የትቀመጠ ገንዘብ ከቼኪንግ አካውንት ገንዘብ በተለየ መልኩ እንዳይንቀሳቀስ ባንኮች ይፈልጋሉ። ከሌሎች የቁጠባ ግልጋሎቶች በተሻለ ፍጥነት ገንዘብን ከሴቪንግ አካውንት ማውጣት ቢቻልም፣ ነገር ግን እንደ ቼኪንግ አካውንት አይፈጥንም፡ ባንኮችም ከሴቪንግ አካውንት ያለን ገንዘብ ለደንበኞቻቸው በመቅጽበትና በተፈለገ ቁጥር የመስጠት ግዴታ የለባቸውም።

የሴቪንግ አካውንት ወለድ ምሳሌ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አንድ ሰው በየወሩ 50 ብር እቤቱ ቢያጠራቅም፣ በአንድ አመት ውስጥ 600 ብር ያኖራል ማለት ነው።

ነገር ግን ይሄው ሰው በየወሩ 50 ብር ባንክ ሴቪንግ አካውንት ውስጥ ቢያኖርና ባንኩ 5% ወለድ ቢከፍለው፣ በአንድ አመት ውስጥ 614 ብር ይኖረዋል ማለት ነው። የሚሰላውም በጂዎሜትሪክ ድርድር ቀመር ነው።

እርግጥ ነው፣ የሴቪንግ አካውንት ወለድ በጣም አንስተኛ ነው፣ ዋናው ጥቅሙ ገንዘብን ከሌሎች የቁጠባ አይንቶች በተለይ መልኩ በፍጥነት ማዘዋወር ማስቻሉ ነው።