አራዴዎን (ዕብራይስጥ፦ አርዋዲ) ከከነዓን ልጆች አንዱ ነበረ። በፊንቄ ደሴት ላይ አራድ (አርዋድ በአሁኑ ሶርያ) የተባለው ከተማ ስሙን ከርሱ እንዳገኘው ይባላል።
አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው፣ በኩሽ ንጉሥ ሓር (ሆርካም) 15ኛ ዓመት ረሃብ በእስያ ስለ ደረሰ፥ ከዚሁ አርዋዲ ልጆች መካከል አንዱ አይነርና ሚስቱ እንተላ ከከነዓን አገር ፈልሰው ወደ ኩሽ መንግሥት ገቡ፣ በደጋም ሲኖሩ የቅማንት ብሔር ወላጆች ሆኑ።