Jump to content

ዘይላ

ከውክፔዲያ
ዘይላ
ዘይላ is located in Somaliland
{{{alt}}}
ዘይላ

11°21′ ሰሜን ኬክሮስ እና 43°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ዘይላ ከደቡባዊ ጅቡቲ ጠረፍ አጠገብ በሱማሊ ላንድ የሚገኝ ታሪካዊ የባህር ወደብ ነው።

በ50 ዓም ገደማ በግሪክኛ በተጻፈው «የቀይ ባሕር ጉዞ» ዘንድ፣ ከአክሱም መንግሥት ጠረፍ በኋላ ከተገኙት የ«በርበሮች» ነጻ ከተሞች፣ መጀመርያው «አባሊቴስ» (የአሁን ዘይላ) ነበረ።

«መጀመርያው አባሊቴስ ይባላል፤ ወደዚህ ቦታ ከአረቢያ አሻግሮ ከሁሉ አጭሩ ጉዞ ነው። እዚህም አነስተኛ «አባሊቴስ» የተባለ ገበያ መንደር ነው፣ በመርከብ ወይም በታንኳ ሊደርስ አለበት። ወደዚህ ቦታ የሚገቡ የንግድ ሸቀጦች፦ ስርጉድ ምስሪት፣ የወይን ጭማቂ ከዲዮስፖሊስ (በይሁዳ ክፍላገር)፣ ለበርበሮች የተዘጋጀ ጨርቅ፣ ስንዴወይን ጠጅ፣ ጥቂትም ቆርቆሮ ናቸው። ከዚህም ቦታ የሚወጡት የንግድ ሸቀጦች፦ ቅመማቅመም፣ ጥቂት የዝሆን ጥርስ፣ የኤሊ ቅርፊት፣ ከሁሉም የተመረጠ በጣም ጥቂት ከርቤ ናቸው፤ አንዳንዴም በርበሮቹ እራሳቸው በታንኳ አሻግረው ወደ ኦኬሊስሙዛ (በአሁን የመን) ያደርሱታል። በዚህም ቦታ የሚኖሩ በርበሮች እጅግ አዋኪዎች ናቸው።»