Jump to content

የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት

ከውክፔዲያ

የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥትጥንታዊ ግብጽ ታሪክ በሰፊው እስከ 8ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ድረስ የነበረበት ጊዜ ነው። በተለይ ከ3ኛው ሥርወ መንግስት እስከ 6ኛው ሥርወ መንሥስት መጨረሻ ድረስ ያለው ዘመን ወይም ከፈርዖን ነጨሪኸት እስከ 2 መረንሬ ድረስ በአሁኑ ሊቃውንት ዘንድ ጥንታዊው መንግሥት ወይም ብሉይ መንግሥት ተብሏል። ነገር ግን እነዚህ ሥርወ መንግሥታት አከፋፈል ጸሐፊውን ማኔቶን በመከተል ናቸው እንጂ ሁልጊዜ አዲስ ቤተሰብ የገባበት አይመስልም።

እነዚህ ፈርዖኖች የራሳቸውን ወገን «የሔሩ (ሆሩስ) ወገን» ይሉት ነበር። ሆኖም በ2ኛው ሥርወ መንግሥት ፐሪብሰን ወገኑን ከሔሩ ወደ ሴት ወገን እንደ ቀየሩ ይመስላል፤ ተከታዩም ኃሰኸምዊ ለሁለቱ ወገኖች ወከለ።

ታላላቆቹ ሀረሞች (ፒራሚድ) እና የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ4ኛው ሥርወ መንግሥት ተገነቡ። በመካከለኛው ዘመን እስላማዊ ጸሐፊዎች እንደ ግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና ፋርሳውያን አል-ታባሪሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ዘንድ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከማየ አይህ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች (የቃየልና የሴት ልጆች) ነበር ብለው ጻፉ። የምጽራይም ልጆች ከጊዜ በኋላ (9ኛው ሥርወ መንግሥት) ሠፈሩበት ብለው ጻፉ። እንዲሁም በኢትዮጵያ አፈ ታሪክ ከማየ አይኅ በፊት በነገሱት ነገደ ኦሪ ወይም ኦሪታውያን ስሞች መካከል የነዚህ ፈርዖኖች ስሞች ሊታዩ ይቻላል፤ በተለይ ፈርዖን ስነፈሩ በንጉሡ ሰነፍሩ ይታያል።

ያም ሆነ ይህ እነዚህ ፈርዖኖች በተለይ ጨካኝና መረኖች እንደ ሆኑ፣ ሁላቸውም እንደ ጠፉ ሊጠራጠር አይችልም። ብዙ ቋንቋ በጽሑፍ በኩል አወረሱ።