ፈርዖን
Appearance
ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ «ፐር-ዓ» ከ«ፐር» (ቤት) እና «ዓ» (ታላቅ) ወይም «ታላቁ ቤት» ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ. በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ንገሥታት ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት በአብርሐም፣ በዮሴፍ ወይም በሙሴ ዘመን የነበሩት ነገሥታት ደግሞ «ፈርዖን» ተብለዋል። ነገር ግን በታሪክ ላይ ፈርዖን የሚለው ማዕረግ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንቱ የግብጽ መንግሥት ከ 2691-2625 ሳይሆን አሊያም በመካከለኛው የግብጽ መንግሥት ከ 2050-1710 ሳይሆን በአዲሱ የግብጽ መንግሥት በ 1570 ነው። ቁርኣንም ፈርዖን ማለት የጀመረበት በአዲሱ የግብፅ መንግሥት በሙሴ ዘመን ነው።
- ደግሞ ይዩ፦ የፈርዖኖች ዝርዝር