ፓምባ
Appearance
ፓምባ በአንድ ባቢሎናዊ ጽላት ዘንድ በአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን ዘመን የሐቲ ንጉሥ ነበር። ናራም-ሲን ፓምባንና የ፲፮ ሌሎች ነገሥታት ትብብር እንዳሸነፋቸው ይመዘገባል። ከነዚህ ነገሥታት ለፓምባ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ምክንያት ይህ ጽላት የሐቲ ሕልውና በናራም-ሲን ወቅት (2049-2030 ዓክልበ. ግድም ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ይመሰክራል። ሆኖም የጽላቱ ቅጂ ከዚያ ዘመን በኋላ (1400 ዓክልበ. ግድም) ተደረገ።
ከፓምባ ጋር ከተባበሩት ሌሎቹ ነገሥታት መካከል የኩጣ ንጉሥ አንማና-ኢላ፣ የፓኪ ንጉሥ ቡናን-ኢላ፣ የኡሊዊ ንጉሥ ላፓና-ኢላ፣ የካነሽ ንጉሥ ዚፓኒ፣ የአሙሩ ንጉሥ ሑዋሩዋሽ፣ የማርሃሺ ንጉሥ ቲሸንኪ፣ የላራክ ንጉሥ ኡር-ላራክ፣ የኒኪ ንጉሥ ኡር-ባንዳ፣ የቱርኪ ንጉሥ ኢልሹናኢል፣ የኩሻራ ንጉሥ ትሽቢንኪ፣ የአርማኒ ንጉሥ ማዳኪና ናቸው። ለአንዱ ስም «ኑር-...» ብቻ ሊነብብ ይችላል፤ አንዳንድ ጸሐፊ ይህ ከታላቁ ሳርጎን ዘመን የነገሠው የቡሩሻንዳ ንጉሥ ኑርዳጋል ይሆናል ብሎአል። ነገር ግን ለዚያው መታወቂያ ማስረጃ የለም።